SKIP TO MAIN CONTENT

ቴዲ አፍሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ቅዳሜ ሊሰጠው ነው

*** የድምፃዊው አድናቂዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ደስታቸውን እየገለፁ ነው

Singer Tewodros Kassahun.
Singer Tewodros Kassahun. Source: University of Gondar

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

ቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ቅዳሜ ሊሰጠው ነው

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ለSBS አማርኛ እንደገለፁት ለድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጠው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ዛሬ ወስኗል ብለዋል።

በዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን እንደሚቀበል የገለፁት ዶክተር አስራት ዩኒቨርሲቲያችን ለዚህ የአገር ባለውለታና " ፍቅር ያሸንፋል" ለሚለው መርሁ ተገቢውን ክብርና  እውቅና በመስጠቱ ታላቅ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

ለድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲው ቴዲ አፍሮ ላበረከተው ሙያዊ አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬት ዕውቅና ሊሰጠው መሆኑን በተመለከተ መረጃው ይፋ ከተደረገበት ቅፅበት አንስቶ አድናቂዎቹ በሶሻል ሚዲያ ደስታቸውን እየገለፁ ነው።

[ ደመቀ ከበደ ፣ አዲስ አበባ ]


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now