SKIP TO MAIN CONTENT

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አህጉራዊ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

*** የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የ2022 የአፍሪካ ስመጥር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ሽልማትን አሸንፈዋል።

News
Source: EthTelecom

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

ዘ ቢዝነስ ኤክዚኪዩቲቭ የተሰኘ በጋና የሚገኝ የፓን ዌስት አፍሪካ ሚዲያ በሞሪሽየስ ባዘጋጀው የ2022 የአፍሪካ ስመጥር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ በአፍሪካ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን አወዳድሯል።

ለ17ቱ የተባበሩት መንግሥታት ዘላቂ የልማት ግቦች (UN-Sustainable Development Goals) በአፍሪካ ለሚኖረው ስኬት ላደረጉት አስተዋጽኦ በየዘርፋቸው አወዳድሮ ነው የሸለመው፡፡

በቴሌኮሙዩዩኒኬሽን ዘርፍ የሞሮኮው፣ ማሮክ ቴሌኮም፣ የኬንያው ሳፋሪኮም፣ የግብፁ ኢትሳላት እንዲሁም የኢትዮጵያው ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።

በዚህም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የ2022 የአፍሪካ ስመጥር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ "በሽልማቱ የኩባንያችንም የሀገራችንም ኩራት መሆናቸውን አስመስክረዋል" ብሏል።

[ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ]


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now