SKIP TO MAIN CONTENT

"ባንኮች 1.8 ቢሊየን ብር ተመዝበረዋል" ዐቃቤ ሕግ

*** በባንኮች ላይ በሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተነሳ 1.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ ምዝበራ በባለፉት አራት አመታት ማጋጠሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

News
Birr, Ethiopia. Source: Giovanni Mereghetti/UCG/Universal Images Group via Getty Images

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓም በሸራተን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት፣ ከደረሰው ምዝበራ ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ ምዝበራው የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው።

በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣ ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው።

ሪፖርተር


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now