Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የ2019 በጀት ዓመት 2.34 ትሪሊዮን ብር የፌዴራል መንግስት በጀት ለፓርላማ ተመራ

የቀረበው ረቂቅ በጀት 2.339 ትሪሊዮን ብር ሲሆን፣ ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ400 ቢሊዮን ብር ገደማ ጭማሪ እንዳለው ተመልክቷል።

Budget.png
Credit: Getty Images

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 2.34 ትሪሊዮን ብር የፌዴራል መንግስት በጀት በማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገለጸ።

የቀረበው ረቂቅ በጀት 2.339 ትሪሊዮን ብር ሲሆን፣ ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ400 ቢሊዮን ብር ገደማ ጭማሪ እንዳለው ተመልክቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ ሁለት ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፣ ከእነዚህ አንዱ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ነው።

ረቂቅ በጀቱ የተዘጋጀው የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ አካል በሆነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ፣ የ2019-2023 የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፍ እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ መሆኑ ተጠቅሷል።

 በበጀቱ ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚውል 2,339,268,126,738 ብር መመደቡ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀት አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ አስፈላጊ ግብአቶችን በማከል ሰነዱ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።


1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now