የተከዜ ድልድይ መፍረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገለጠ።
የመረጃ ማጣሪያው "የትግራይ አርሶ አደሮች የግብርና ሥራቸውን እዲያከናውኑ ለመደገፍ የወጣውን የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ውድቅ ያደረገው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት የተከዜ ድልድይን ሆን ብሎ" አፍርሷል ብሏል።
በሕወሓት በኩል እስካሁን ይፋ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልተሰጠም።
የተከዜ ድልድይ እንዳባጉናና ማይፀምሪን የሚያገናኝ ነው።
የድልድዩን መሰበር እውነታነት አስመልክቶ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ የደቡባዊና ምሥራቃዊ አፍሪካ ቢሮ የገለጠ ሲሆን፤ አያይዞም ሰብዓዊ እርዳታውን በእጅጉ አስከፊ የሞት ሽረት ሁኔታ ለሚገኙ ሰዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በእጅጉ ያሳሳበው መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኞ ጁን 28 የተናጠል ተኩስ ማቆም እወጃ ማድረጉ ይታወሳል።

