የትግራይ ክልል ም/ቤትና ካቢኔ ሕጋዊ ሰውነት ስለሌለው የፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ እንደማይደረግለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለፀ

*** የውሳኔው አፈፃፀምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥናት ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል

Adam Farah

Adam Farah, Speaker of the House of Federation Source: HoF

የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚው አካል/ካቢኔ/ ህገመንግስታዊ ቅቡልነት ስለሌላቸው ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ህጋዊ ግንኙነት ማድረግ እንደማይችሉም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባሄ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡

ይህም በመሆኑም ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ከትግራይ ክልል ከፍተኛ አስፈፃሚ አካላት ጋር እንደህጋዊ አካላት በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ የፌዴራል ተቋማት ለክልል ተቋማት የሚሰጧቸውን ድጋፎች መስጠት፣ በፌዴራል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ የመሳሰሉ ጉዳዮችን ማድረግ አይቻልም ብለዋል፡፡

በአንጻሩ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ ፣ወረዳ ፣ ከተማ ካሉ ህጋዊ የክልሉ መዋቅር ጋር ብቻ ግንኙነቱ እንደሚደረግና ይህም በሚዋቀር ኮሚቴ ክትትል እንደሚደረግ አቶ አደም ፋራህ በተለይ ለኢቲቪ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ውሳኔ ሊደረስ የቻለው የትግራይ ክልል መንግስትና ገዥው ፓርቲ ህውሃት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ባከበረ መልኩ የስራ ዘመኑ በምክር ቤቱ ውሳኔ የተራዘመውን የክልሉን ምክር ቤት የህግ አስፈፃሚ አካል ወደ ቦታው መመለስ ስላልቻሉ ነው ብለዋል አፈ ጉባኤው፡፡

ውሳኔው የትግራይ ህዝብ ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ እየተከተለ ባለ ቡድን ምክንያት ከሰላም፣ልማትና መሰረታዊ አገልግሎት አንፃር እንዳይጎዳና የትግራይ ህዝብ እንደሌሎች የአገራችን ህዝቦች መሰረታዊ የልማትና የደህንነት አገልግሎቶች እንዲያገኙ ታስቦ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡

‹‹ይሄ ሊሆን የቻለው ለትግራይ ህዝብ ካለን ክብር ነው›› ያሉት አፈ-ጉባሄው፤‹‹ ህዝብም እንደ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች ሊያገኘው የሚገባውን ጥቅም ሊከበርለት ይገባል ከሚል ጽኑ እምነት የመነጨ ነው›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የውሳኔ አፈፃፀምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥናት ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል፡፡

በህገወጥ መንገድ የተቋቋመው የትግራይ ምክር ቤትና ካቢኔ ህጋዊ ሰውነት ስለሌለው የፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ እንደማይደረግለትም ተመልክቷል፡:

በቀጣይ በክልሉ ካሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በተለይ ህዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ በጥናት ተመስርቶ ተፈፃሚ ይደረጋልም ተብሏል፡፡

 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now