ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ

*** የፌደራል መንግሥት የትግራይ ሕዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

House of Federation

Source: HoFC

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡

ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ በትናንት ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ ያቻለው፡፡

ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ሶስት ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል፡፡

የመጀመሪያው የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡

ሁለተኛው የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

ሶስተኛ የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ ተላልፏል።

(ኢብኮ)


1 min read

Published

Updated

By Stringer


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now