SKIP TO MAIN CONTENT

የቶኪዮ ኦሎምፒክ መክፈቻ ነበልባል በጃፓናዊቷ የቴኒስ ኮከብ ናኦሚ ኦሳካ ተለኮሰ

63 አትሌቶችን ያሰለፈችው አውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በኬት ካምፕቤልና ፓቲ ሚልስ በኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ሲውለበለብ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በአብደልማሊክ ሙክታር ተውለብልቧል

Tokyo 2020 Olympic Games
Naomi Osaka of Team Japan lights the Olympic cauldron with the Olympic torch during the Opening Ceremony of the Tokyo 2020 Olympic Games. Source: Getty

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

ዓርብ ምሽት በተካሔደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020 የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የኦሎምፒክ ጅማሮ ብሥራት የሆነው ነበልባል በጃፓናዊቷ የቴኒስ ኮከብ ተለኩሷል።

የዘንድሮው ኦሎምፒክ ምንም እንኳ ባለፈው ዓመት መካሔድ ቢኖርበትምና ስታዲየሞቹም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተመልካች አልባ የኦሎምፒክ ውድድሮችን ቢያካሂዱም ተስፋ፣ ባሕልና ዝንቅነትን አቅፏል።

Naomi Osaka
Naomi Osaka. Source: N.Osaka

በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ወቅት አትሌቶች በኦሎምፒክ ስታዲየም የተመሙት የፊት ጭምብል አጥልቀው ነበር። 

የየአገራቱን ሰንደቅ ዓላማዎች የሚያውለበልቡ አትሌቶች ብቅ ሲሉ እንደቀድሞው በሆታ የደመቀ አቀባበል ሳይሆን የጠበቃቸው በፀጥታ የተዋጠ ስታዲየም ነው። 

Michezo ya Olimpiki Tokyo 2020
Flag bearers Cate Campbell and Patty Mills of Team Australia during the Opening Ceremony of the Tokyo 2020 Olympic Games in Tokyo. Source: Visual China Group via Getty
Tokyo 2020 Olympic Games
Flag bearer Abdelmalik Muktar of Team Ethiopia during the Opening Ceremony of the Tokyo 2020 Olympic Games at Olympic Stadium on July 23, 2021 in Tokyo, Japan. Source: Getty

በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ የጃፓን ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ የተገኙ ሲሆን፤ የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ቶማስ ባኽ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር "ዛሬ የተስፋ ወቅት ነው። እውነት ነው፤ ሁላችንም አስበነው ከነበረው በተለየ መልኩ በጣሙን የተለየ ነው። ይሁንና በስተመጨረሻ ሁላችንም እዚህ ተሰባስበን እንገኛለን" ብለዋል።

Tokyo 2020 Olympic Games
Fireworks light the sky during opening ceremonies at the 2020 Tokyo Olympics. Source: Getty

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now