SKIP TO MAIN CONTENT

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰማ

*** ዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC እና ሮይተርስ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተሰጣቻው መካከል ይገኙበታል

Media
Source: Getty Images

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰማ።

እርምጃ እየተወሰደባቸው የሚገኙት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ዓለም በተሳሳተ መንገድ እንዲያውቀውና በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲበረታ በማድረጋቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደተናገረው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ወቅታዊውን ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲሁም በሞያዊ ስነ ምግባር እንዲዘግቡ ማሳሰቢያ ቢሰጣቸውም በእንቢተኝነት በቀጠሉት ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

ዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC ፣ ሮይተርስ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተሰጣቻው መካከል ይገኙበታል።

"ሮይተርስ" ከትላንትና ወዲህ በሀገር ውስጥ ያላቸው ዘጋቢ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ፣ ዘገባዎችን ፣ ዜናዎችን እንዳትሰራ ሙሉ በሙሉ እንደታገደች የብሮድካስት ባለስልጣን ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now