የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሯል - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

*** ለበዓሉ ስኬታማነት ትብብር ላደረጉ ምስጋና ቀርቧል

Irecha

Source: PD

አባገዳዎች ፣ አደ ስንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተከበረው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዕቅድ በማውጣት እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎቹን በማወያየት ወደ ስራ መግባቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ ልዩ ልዩ አካላትን ያሳተፍ የፀጥታ ስራ በመሰራቱ በዓሉን በሰላም ማክበር እንደተቻለ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ለበዓሉ ስኬታማነት ትብብር ላደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የበዓሉ ተሳታፊዎች እና የፀጥታ አካላት በሙሉ ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

 


1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now