ብሪስበን የ2032 የኦሎምፒክና ፓራኦሎምፒክ አስተናጋጅ ሆና ተመረጠች *** የብሪስበን የኦሎምፒክ አስተናጋጅ ሆኖ መመረጥ አውስትራሊያን ቀደም ሲል ኦሎምፒክን በሶስት ከተሞች ካስተናገደችው ዩናይትድ ስቴትስ ጎን አሰልፏታል። 1 min read
Published 21 July 2021 7:15pm
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Skip to article content Share this with family and friends
ብሪስበን የ2032 የኦሎምፒክና ፓራኦሎምፒክ አስተናጋጅ ከተማ ሆና በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተመረጠች።
የብሪስበን የኦሎምፒክ አስተናጋጅ ሆኖ መመረጥ አውስትራሊያን ቀደም ሲል ኦሎምፒክን በሶስት ከተሞች ካስተናገደችው ዩናይትድ ስቴትስ ጎን አሰልፏታል።
አውስትራሊያ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበትን ኦሎምፒክ ባዘጋጀችው ሜልበርንና ሲድኒ ከተሞች የበጋ ኦሎምፒኮችን አስተናግዳለች።
Qld Premier Annastacia Palaszczuk (center). Source: Getty በዛሬው ዕለት የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ እና የአውስትራሊያ ልዑካን ቡድን አባላት ለዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የመጨረሻ የብሪስበንን ምረጡ ዝግጅታቸውን አቅርበዋል።
Source: A.Palaszczuk የዓለም አቀፉን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ውሳኔ በጉጉት በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሲጠባበቁ የነበሩ የብሪስበን ነዋሪዎችም ደስታቸውን ገልጠዋል። ርችትም ተተኩሷል።
Spectators celebrate after Brisbane was announced the host of the 2032 Olympics during the announcement of the host city for the 2032 Olympic Games. Source: Getty