SKIP TO MAIN CONTENT

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝና ዋና አዘጋጁ ምስጋን ዝናቤ ታሰሩ

*** የጋዜጠኞቹን መታሰር አስመልክቶ በወቅቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰጠ ይፋ መግለጫ የለም

Journalist Temesgen Desalegn
Journalist Temesgen Desalegn Source: PD

1 min read

Published

Updated

By Demeke Kebede


Skip to article content

የተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ እንዳለው ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓም ከሰዓት በኋላ በርከት ያሉ ፖሊሶች ቢሮአቸው ድረስ በመምጣት ለጥያቄ እንደሚፈለጉ ገልፀው ይዘዋቸው እንደሄዱ ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰራቸውን  ከፖሊሶች እንደተነገራቸው ጨምሮ ገልጿል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቀደመው የኢህአዴግ አገዛዝ ወቅትም ይሁን አሁን በለውጡ ወቅት የሰሉ ትችቶችን በመፃፍ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በላይ ጊዜያት ውስጥ የብዙኃን መገናኛ ብዝኅነት ቢፈጠረም የጋዜጤኞች መረጃ የማግኘት መብት አለመከበሩ ተገለጧል።

የጋዜጠኞች መረጃ የማግኘት መብት አለመከበር በተግዳሮትነት የተነሳው የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በውይይቱ ወቅት የብዙኅን መገናኛ አስተዳደር ሕጎችና ፖሊሲዎች ቢወጡም በተገቢ መልኩ ሥራ ላይ አለመዋላቸው ተነገሯል። 

በውይይቱ ተሳታፊዎች የማሻሻያና ማጎልበቻ ምክረ ሃሳቦች ቀርበዋል። 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now