SKIP TO MAIN CONTENT

የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤና ሌሎች ተጠርጣሪ የነበሩ ተከሳሾች በዋስ ተለቀቁ

*** እነ አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እስከሚታይ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል  ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ፡፡

በሌላም በኩል፤ በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩትን ወ/ሮ ሕርቲ ምህረተአብና የትግራይ ክልል መንግሥት አማካሪ የነበሩት ወልደ ጊዮርጊስ ደስታ፣ በእነ አቶ ዓባይ ወልዱ የክስ መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት አምደማርያም ተፈራ እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወስኗል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር በወንጀል ተፋላጊ መሆናቸው ተጠቅሶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ተላልፎባቸዋል።

አቶ ስብሐት ነጋን አክሎ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ ቅዱሳን ነጋና ሌሎች  ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን ላስቻለው ፍርድ ቤቱ አመልክቷል።

በአቤቱታውም መሠረት፤ አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እስከሚታይ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now