“የኮንሶ ዞንና አካባቢው ረዘም ላለ ጊዜ ሰላም አጥቶ የቆየበት ችግር ተገቢውን ትኩረት አላገኘም” - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

*** በኢሰመኮ ሪፖርት እንደተመለከተው ቢያንስ 66 ሰዎች ተገድለዋል፣ 39 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ብዙ ቤቶችና ንብረት በእሳት ተቃጥለዋል፤ እንዲሁም ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።

EHRC Konso

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of Ethiopian Human Rights Commission. Source: EHRC

ኮንሶ ዞን፡ በተደጋጋሚ የሚያገረሹ ግጭቶችና  የሰብአዊ መብቶች ቀውስ የተፈናቀሉና የተጎዱትን ማቋቋም አፋጣኝ ትኩረት ይሻል በደቡብ ክልል፣ የኮንሶ ዞን ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ዳግም ባገረሹ ተከታታይ ግጭቶች የደረሰው አሰቃቂ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት፤ የአካባቢው ሰብአዊ ቀውስ ዘላቂ እልባት ባለማግኘቱ እየተባባሰ መሄዱን እንደሚያሳይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከኅዳር 12 ቀን እስከ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በሀይበና እና በአይዴ ቀበሌዎች፣ በአርባምንጭ፣ በጊዶሌ እና በካራት ከተማዎች ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የፈጣን ዳሰሳ ሪፖርት ነው (ኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም. በኮንሶ ዞን አካባቢ ባገረሸው ግጭት መነሻነት በአካባቢው ስላለው ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ የተደረገ ፈጣን ምርመራ ሪፖርት) ።

በሪፖርቱ እንደተመለከተው ቢያንስ 66 ሰዎች ተገድለዋል፣ 39 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ብዙ ቤቶችና ንብረት በእሳት ተቃጥለዋል እንዲሁም ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹የኮንሶ ዞን እና አካባቢው ረዘም ላለ ጊዜ ሰላም አጥቶ የቆየበት ችግር ተገቢውን ትኩረት አላገኘም። በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከመኖሪያው መፈናቀሉና ከመካከላቸው ለአምስተኛ ጊዜ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች ጭምር መኖራቸው አሳዛኝ የሰብአዊ መብቶች  ቀውስ ነው። ስለሆነም ለተፈናቃዮች በአፋጣኝ አስፈላጊውን ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር፣ የፌዴራሉና የክልሉ መንግሥታት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ተቀናጅተው  ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል›› ብለዋል።

 


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now