"አውስትራሊያን ልዩ ከሚያደርጓት አንዱ መድብለባሕላዊነቷ ነው" - አንቶኒ አልባኒዚ

***የቪክቶሪያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ስድስት ወራት ተራዘመ

Press conference

Senator Christina Keneally (L), Anthony Albanese, Leader of the Opposition (C) and Andrew Giles MP Source: Courtesy of ALP

ዛሬ ረቡዕ ሴፕተምበር 2 - 2020 የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኒዚ በጠሩት የባሕላዊና ቋንቋ ዝንቅ ሚዲያ ጋዜጣዊ መግለጫ "አውስትራሊያን ልዩ ከሚያደርጓት አንዱ መድብለባሕላዊነቷ ነው" ሲሉ ገልጠዋል።

አቶ አልባኒዚ በዚሁ በዌቢናር በተካሔደ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት የአውስትራሊያ ምጣኔ ሃብት ወደ ድቀት ማምራቱን፣ አረጋውያን በመጠወሪያ ቤቶቻቸው የተሟላ ክብካቤ አለማግኘት፣ እንዲሁም የሥራጠባቂና ሥራጠያቂ ድጎማን አስመልክተው ተናግረዋል።

የመድብለባሕል ሚዲያ ተቋማት በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የከፋ ጎጂነት፣ ቅድመ መከላከል፣ ተከታታይ የጥንቃቄ መመሪያዎችንና ድንጋጌዎችን እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋቸው ለሆኑ የማኅበረሰብ አባላት ተገቢውን መረጃ በመስጠቱ ረገድ እያበረከቱ ያሉትን አስተዋፅዖዎች አንሰተው አመስግነዋል።

በታካይነትም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የታደሙት አንድሩ ጂልስ - የሌበር መድብለባሕል ቃል አቀባይ የመድብለባሕል ማኅበረሰባት ለአውስትራሊያ ያበረከቱትን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች ነቅሰው አድናቆታቸውን ገልጠዋል። 

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት በተለይም የአረጋውያን በመጠወሪያ ቤቶቻቸው ተገቢውን ክብካቤ አለማግኘት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። 

ይህንኑ አስመልክቶ የሜልበርን ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ኤሊዛቤት እናታቸው በኮቪድ-19 ተጠቅተው ተገቢውን ክብካቤ አለማግኘታቸውንና አሁንም ሆስፒታል ተኝተው ሕክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። 

ወ/ሮ ኤልዛቤት እናታቸው በጠና ታምመው ባሉበት ወቅት እሳቸው ብርቱ ግፊት አድርገው ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ባያደርጉ ኖሮ ምናልባትም እናታቸው እስካሁን በሕይወት አይቆዩ እንደነበር፣ የአረጋውያን መጠወሪያ የጤና ሠራተኞች የስልጠና፣ የቋንቋና የተሟላ የተጋላጭነት መከላከያ ቁሳቁሶች እንደሌላቸው አመላክተዋል።

አያይዘውም፤ ባለፈው ወርሃ ኦገስት የጤና ሠራተኞች የአረጋውያኑን ሃፍረተ ስጋ ያጸዱበትን የእጅ ጓንት ሳይቀይሩ ምግብ ለአረጋውያኑ ሲያቀርቡ መመልከታቸውን ገልጠዋል። 
CALD Press conference
Elizabeth Source: Courtesy of PD


አቶ አልባኒዚም በበኩላቸው ለአረጋውያን መጠወሪያ የጤና ሠራተኞች በቂ ስልጠናና የሠራተኛ ኃይል እንደሌለ ከቶውንም የአረጋውያን የጤና ሠራተኞች ዘንድ በእጅ ጓንት እጥረት ሳቢያ የቀኝ ወይስ የግራ እጅ ጓንት በሚል እስከማስመረጥ የተደረሰበትን ሁኔታ ጠቅሰዋል።

በወ/ሮ ኤልዛቤት እናትና በመሰል አረጋውያን ላይ እየደረሰ ስላለው አሳዛኝ ሁኔታ እንዲገታ ኃላፊነት ያለበት ፌዴራል መንግሥት በብቃት አለመወጣትንም አንስተዋል። 

በተጨማሪም ዌቢናሩን ሲመሩ የነበሩት ሴናተር ክሪስቲና ኬኔሊ - የሌበር የአገር ውስጥ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ከአረጋውያን መጠወሪያ ጋር በተያይዘ የፌዴራል መንግሥቱ ላይ ብርቱ ትችት ሰንዝረዋል።

ቫይረስ

ቪክቶሪያ ውስጥ በዛሬው ዕለት 90 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ስድስት ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

ሕይወታቸውን ካጡት ስድስት ቪክቶሪያውያን ውስጥ አምስቱ ሴቶች ዕድሜያቸው በ80ዎቹ አንድ ወንድ በ90ዎቹ የነበሩ ናቸው።

 ይህ በእንዲህ እንዳለም ዛሬ ጠዋት የቪክቶሪያን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በስድስት ወራት ለማራዘም እንዲቻል የፓርላማ ይሁንታን አግኝቷል።

ድንጋጋጌው ያለፈው 20 የድጋፍና 19 ተቃውሞ ገጥሞት በአንድ አብላጫ ድምፅ ነው።

እስካሁን ግብር ላይ ውሎ ያለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሴፕቴምበር 13 ያከትማል።

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ እሑድ ሴፕቴምበር 6 ለቪክቶሪያ ገጠርና ከተሞች የሚውሉ ሁለት የኮቪድ-19 ገድብ ማላሊያ ፍኖተ ካርታዎችን ይፋ ያደርጋሉ። 

በሌላ በኩል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 17 ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል።


Share

2 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service