ሌበር ፓርቲ የደቡብ አውስትራሊያን ምርጫ አሸነፈ

*** ድል የተነሱት የደቡብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ስቲቨን ማርሻል መንግሥታቸውን ብቻ ሳይሆን ከቶውንም የምክር ቤት ወንበራቸውንም ሊያጡ ይችላሉ።

SA Labor leader Peter Malinauskas during the party's state conference at the Adelaide Convention Centre in Adelaide, Saturday, 27 March, 2022.

SA Labor leader Peter Malinauskas during the party's state conference at the Adelaide Convention Centre in Adelaide, Saturday, 27 March, 2022. Source: AAP

የሌበር ፓርቲ ዛሬ ቅዳሜ ማርች 19 የተካሔደውን የደቡብ አውስትራሊያ ምርጫ አሸንፏል።

የፓርቲው መሪ ፒተር ማሊናዩስካስ 47ኛው የደቡብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ለመሆን በቅተዋል። 

የፌዴራል ሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሪሚየር ማሊናዩስካስ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

News
Source: A.Albanese

ሌበር ፓርቲ የአያሌ መራጮችን ድምፅ ማግኘት በመቻሉ 27 የምክር ቤቶችን አሸንፏል።

የሊብራል ፓርቲ 15 የምክር ቤት ወንበሮችን ያገኘ ሲሆን የግል የምክር ቤት ተወዳዳሪዎች ስድስት ወንበሮችን ለማሸነፍ ችለዋል። 

ሌበር ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ለማቆም ማሸነፍ ይጠበቅበት የነበረው 24 የምክር ቤት ወንበሮችን ብቻ ነበር። 

የሊብራል ፓርቲ መሪ ምናልባትም በሌበር ፓርቲ ተቀናቃኛቸው የዳንስታን የምክር ቤት ወንበራቸውን ሊያጡ ይችላሉ። 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now