SKIP TO MAIN CONTENT

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሹራ ቂጣታ 40ኛውን የወንዶች ለንደን ማራቶን አሸነፈ

*** አትሌት ሞስነት ገረመው አራተኛ ወጥቷል

Sports
Shura Kitata Source: REU

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

አትሌት ሹራ ቂጣታ  40ኛውን የወንዶች  ለንደን ማራቶን ሲያሸንፍ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሲሳይ ለማ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

የኢትዮጵያውያ የበላይነት በታየበት የዘንድሮው የወንዶች ውድድር ሙሌ ዋሲሁን 5ኛ እና ታምራት ቶላ ደግሞ 6ኛ ደረጃን አግኝተዋል።

ከአትሌት ኤሉድ ኪፕኦጌ በመቀጠል ውድድሩን የማሸነፍ ቅድመ ግምት አግኝቶ የነበረው አትሌት ሞስነት ገረመው አራተኛ ወጥቷል።

ይህ የለንደን ማራቶን ውድደር በኢትዮጵያውን የበላይነት ተጠናቋል። ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው ኬንያዊው ኪፕቾጌ ሽንፈትን ተጎንጭቷል። ኪፕቾጌ 8ኛ ወጥቷል።

የኤሉድ ኪፕቾጌ ተቀናቃኝ ይሆናል ተብሎ የነበረው ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት አራሱን ማግለሉ አይዘነጋም።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now