ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትናንት በወቅታዊ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መገለጫ ሰጥተዋል።
ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉትን የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የዝግጁነት አቋም ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ፋና እንደዘገበው
ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉት የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአካል አግኝተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡
ሌ/ጄኔራል ባጫ ፥ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸውን ጥቃት አስመልክተው እንደገለጹት ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩ የህወሓት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች ሶስት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ጥቃት ፈፅመዋል ብለዋል ፦
1ኛ. ሠራዊቱን ከውስጥ ማፍረስ፣
2ኛ. ሠራዊቱን መውጋትና
3ኛ. ማዘናጊያ የሽምግልና ስራ መስራት ስለነበር እሱን ተልዕኮ ነው የፈጸሙት ብለዋል።
ሠራዊቱን ከውስጥ ለማፍረስ የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ አዲስ አበባ በሚገኘው የመገናኛ ሀላፊ አማካኝነት ወደነሱ አዙረዋል ብለዋል።
እንዲሁም መከላከያና ጦሩ እርስ በርሱ እንዳይገናኝ አድርገዋል ሲሉ ገልፀዋል።
እነዚህ አካላት የሠራዊቱን የወር ደሞዝ እና ቀለቡን ወስደውበታል፣ አዛዦችንም አፍነዋል ብለዋል።
ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሰራዊቱ ይህ ሁሉ ተፈፅሞበት ተዋግቷቸዋል፣ ጀግንነትም ፈፅሟል ሲሉ ተናግረዋል።
ውጊያው ከክልሉ ልዩ ሀይል ብቻ አልነበረም ያሉት ሌ/ጄኔራል ባጫ ፣ በዛላንበሳ ፣ በሽራሮ ፣ በራማ ፣ በፆረና እና በሌሎች ቦታዎች የኦነግ ሸኔ አባላት ባንዲራቸውን ይዘው አብረው ወግተውናል ብለዋል።
በስፍራው የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ ሠራዊቱን አብረውት እየመሩት እንደሚገኙ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

