መድኃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶችን ጭነው በሕወሓት ተደብቀው የነበሩ አራት የጭነት ተሽከርካሪዎች ተያዙ

*** መድሃኒቶቹና የሕክምና ቁሳቁሶቹ የተያዙት ቆላ ተምቤን ልዩ ቦታው ጉሮሮ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው፡፡

Medical equipments

Source: FANA BC

በሕወሓት ከጤና ተቋማት ተወስደው በአራት ባለተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ ሙሉ ተደብቀው የነበሩ መድሃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  የመከላከያ ጤና መምሪያ አስታወቀ።

የጤና መምሪያው በቁጥጥር ስር የዋሉት መድሃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶች ከሰሜን ዕዝ ሆስፒታልና ከዕዙ ሜዲካል ሎጂስቲክስ የተዘረፉ ናቸው ሲልም ገልጿል፡፡

መድሃኒቶቹና የሕክምና ቁሳቁሶቹ የተያዙት ቆላ ተምቤን ልዩ ቦታው ጉሮሮ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው፡፡

የምዕራብ ዕዝ ጤና መመሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ ከፍያለው እንደገለጹት ሕወሓት ከሰሜን ዕዝ ሆስፒታል ዘርፎ የደበቀው መድሃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ የተያዘው በመከላከያ ሰራዊት አሰሳ ነው፡፡

አያይዘውም፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ በውጊያ ጊዜ የሚያገለግሉ ግላቮች፣ የህመምተኛ መታከሚያ አልጋዎችና የተለያዩ አይነት መድሃኒቶች እንደሚገኙባቸውና መድሃኒቶቹ ለሰሜን ዕዝ ሆስፒታልና ለዕዞች እንደሚከፋፈሉ ተናግረዋል።

ከተያዙት መድሃኒቶች በርካቶቹ ከውጭ አገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የተገዙ በመሆናቸው በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረግ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

** ምንጭ ኢዜአ


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now