በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት እና ካቶሊክ ት/ቤቶች መምህራን የተሻለ ክፍያን እና የስራን ሁኔታን በመጠየቅ ለሰልፍ ወጡ ። ሰልፈኞቹ ከኒው ሳውዝ ዌል በመነሳት ወደ ካንብራ አቅንተዋል ።
የኒውሳውዝ ዌልስ የመምህራን ፌዴሬሽን እና የገለልተኛ ትምህርት ህብረት አውስትራሊያ ፤ በጣምራ በመሆን፤ ሰልፉ በጁን 30 ጀምሮ ለ 24 እንዲደረግ በጋራ ውሳኔ ላይ በመድረሳቸውም ነው ሰልፉ የተጠራው።
ቀያይ ካኒተራዎችን ለብሰው የወጡት ሰልፈኞች በየጊዜው የሚደርሳቸው ሙገሳ ብቻ በቂ ያለመሆኑን ለማሳየት“ ከምስጋና ባላይ ” የሚል መፈክሮችን በጉልህ አሳይተውል ፤ የተሰጣቸውንም 3 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ከስራቸው ጋር ሲነጥጥጸር በቂ ያለምሆኑን ገልጸዋል ።
የኒውሳውዝ ዌልስ የመምህራን ፌዴሬሽን ጭማሪም ከ 5 እስክ 7 በመቶ እንዲሆን ጥያቄ አቀርቧል ።
ባልፉት ስድስት ወራት ለሶስተኛ ጊዜ በተጠራው ሰልፍ ከ 85፣000 በላይ መምህራን ተሳትፈዋል ።
እንዲህ ያለን ሰልፍን ሁለቱ ህብረቶች በጋራ ሲያዘጋጁ በ 25 አመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሮለታል ።
የትምህርት ምኒስትሯ ሳራ ሚቸል ሰልፉ በመካሄዱ የተሰማቸውን ቅሬታን ድርጊቱ ከፖለቲካ አጀንዳ ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ገልጸውታል ።አያይዘውም መንግስት ለህዝብ አገልጋዮች የሚከፍለው ክፍያ የተሻለ ነው ሲሉ የሰልፈኞቹን የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ አጣጥለውታል ።

