"የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አብን ሰልፉን የሰረዘ መሆኑን አውቃችሁ ሰልፎችን ከማስተባበርና ከመምራት እንድትቆጠቡ" - አብን

*** "ሰልፉን አስተባብሮ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት አልተቻለም" - አብን

NAMA protests

Source: NAMA

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል።

በጠራው ሰልፍና ከሰልፉ ጋር ተያይዞ በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው ዛሬ ማምሻውን እስከ ምሽቱ 5:00 ድረስ ውይይት ያደረገ ሲሆን አብን ጠርቶት የነበረውን ሰልፍ በመንግስት አምባገነናዊ ተግባር ሰልፉን አስተባብሮ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት ባለመቻሉ መሰረዙን ይገልፃል።

ስለሆነም የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አብን ሰልፉን የሰረዘ መሆኑን አውቃችሁ ሰልፎችን ከማስተባበርና ከመምራት እንድትቆጠቡ እያሳወቅን ቀጣይ የአብን የትግል አካሄዶችን በተመለከተ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፡ አብን

ጥቅምት 17/2013 ዓም


1 min read

Published


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now