SKIP TO MAIN CONTENT

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል ዶ/ር ጌታሁን ካሣ የሥራ መልቀቂያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ

*** “ዶ/ር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን“ - የምርጫ ቦርድ

NEBE
Dr Getahun Kassa Source: PD

1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል ዶ/ር ጌታሁን ካሣ የሥራ መልቀቂያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ።

ዶ/ር ጌታሁን ከቦርድ አባልነታቸው ለመልቀቅ ግድ ስለተሰኙበት ወይም ስለፈለጉበት ምክንያት “ብዙ ምክንያቶች“ እንዳሏቸው ፍንጭ ከመስጠት ባለፈ ምክንያቶቻቸውን ይፋ አላደረጉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስለ ዶ/ር ጌታሁን የሥራ ተሞክሮዎች ሲገልጽ ይህን አስፍሮ ነበር፤

ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በሞያቸው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከእነርሱም መካከል፥ በትግራይ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህር እና የት/ቤቱ ዲን፣ በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ህግና አስተዳደር ኮሌጅ በመምህርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ቢሮዎች በአማካሪነት፣ በልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአማካሪነት እንዲሁም፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከህግ ባለሞያነታቸው፣ አማካሪነታቸው እና መምህርነታቸው በተጨማሪ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሥር የሚገኘው የህግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ ውስጥ አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዶ/ር ጌታሁንን የሥራ መልቀቂያ አስመልክቶ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን“ ብሏል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now