ሁለት ፓርቲዎች ተሰረዙ፤ አራት ታከሉ

*** የባንክ አገልግሎት በመቀሌ ተጀመረ

NEBE

Birtukan Mideksa, Chairperson of the National Election Board of Ethiopia. Source: Getty

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነ እና የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ ብሎ ባለፈው መግለጫው ከጠቀሳቸው ፓርቲዎች መካከል አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን ሟሟላታቸውንና ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ባለሟሟላታቸው መሰረዛቸውን አስታውቋል።

 - መስፈርት  በማሟላት ያጠናቀቁ 

 

1. የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/- 39%

2. የአፋር ሕዝብ ፓርቲ /አሕፓ/- 45%

3. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ -94%

4. የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ /አነግፓ/ - 48%

- ባለሟሟላታቸው  የተሰረዙ

1.የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /መኦሕዴፓ/ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 % በታች በመሆኑ እና የ1,142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ፣

2. የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ - 778 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ እና በምስክርም መረጋገጡ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ

ቦርዱ ፓርቲዎች በአዲሱ አዋጅ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን የማጣራት ስራ ሲያከናውን ቆይቶ ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ያላቀረቡ 26 ፓርቲዎችን መሰረዙ ይታወሳል።

መቀሌ

ከሰኞ ታህሳስ 19 ጀምሮ በመቀሌ የባንክ አገልግሎት  መጀመሩን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለ ሥላሴ ለኢፕድ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።  

ከንቲባው አያይዘውም የግል ባንኮችም ግልጋሎት መስጠት እንዲጀምሩ መመሪያ የተላልፈላቸው መሆኑን ገልጠዋል።


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now