የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 03 ቀን 2013 ዓ.ም የምርጫ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ምርጫ ቦርድ ባወጣው 6ተኛው አገር አቀፍ የምርጫ ሰሌዳ ላይ በተገለጸው መሰረት የካቲት 03 ቀን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ ቀን ነው።
ቦርዱ የምርጫ ምልክት በመውሰድ ለምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በፍላሽ እንዲደርሳቸው ያደረገ ሲሆን በተጨማሪም በድረ-ገጹ ላይ አስፍሯል።
በዚህ መሠረት:-
✔በአዲስ አበባ ከተማ - 1,848
✔በሲዳማ ክልል - 2,247
✔ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 699
✔አፋር ክልል- 1,432
✔አማራ ክልል- 12,199
✔ድሬዳዋ ክልል- 305
✔ጋምቤላ ክልል- 431
✔ሃረሪ ክልል- 285
✔ኦሮሚያ ክልል- 17,623
✔ደ/ብ/ብ/ህ ክልል- 8,281
✔ሶማሌ ክልል- 4,057
በአጠቃላይ 49,407 የምርጫ ጣቢያዎች ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

