የ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' BLM ሕዝባዊ ንቅናቄ ለ2021 የኖቤል ሰላም ሽልማት ታጨ

*** ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በ Black Lives Matter ከተካሄዱት ሰልፎች ውስጥ 93 ፐርሰንቱ ሰላማዊ ነበሩ።

BLM

A mural painted by artist Kenny Altidor depicting George Floyd is unveiled on a sidewall of CTown Supermarket on July 13, 2020 in New York City. Source: Getty

የ 'Black Lives Matter' - BLM ሕዝባዊ ንቅናቄ  የዘር ኢ-ፍትሐዊነትን በመፋለም ረገድ "በመላው ዓለም ያካሔደው ንቅናቄ በጣሙን ጠቃሚ ነው" በሚል አመኔታ በኖርዌይ ፓርላማ አባል ፒተር ኢድ በሰብዓዊ ክብር ዘርፍ ለኖቤል ሰላም ሽልማት ታጭቷል።

 የሕዝባዊ ንቅናቄውን ሂደት አስመልክተው ሲናገሩም "ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኛዎቹ በብላክ ላይቭስ ማተር የተካሄዱት ሰልፎች ሰላማዊ ነበሩ" ብለዋል።

አያይዘውም " እርግጥ ነው፤ ግጭቶች ነበሩ። ሆኖም አብዛኛዎቹ የተከሰቱት አንድ በፖሊስ አለያም በጸረ-ሰላማዊ ሰልፈኞች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ የትጥቅ ግጭት አካባቢና ኩነት ዳታ ፕሮጄክት የሴፕቴምበር ጥናት መረጃ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከተካሄዱት ሰልፎች ውስጥ 93 ፐርሰንቱ ሰላማዊ ነበሩ።

BLM
A vigil was held in Cushing Square in Belmont for alleged hate crime victim Henry Tapia, who was run over by a vehicle in a road rage incident. Source: Getty

የኖቤል ሰላም ሽልማት ኮሚቴ የዕጩዎች ጥቆማ መቀበልን በፌብሪዋሪ 1 ያቆማል፣ በማርች ሁነኛ ተፎካካሪ ያላቸውን ዕጩዎች ይወስናል፤ በኦክቶበር ከዕጩዎቹ መካከል አሸናፊ ያለውን መርጦ በማስታወቅ ዲሴምበር 10 የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን ያካሂዳል።

ባለፈው ዓመት 300 ዕጩዎች ለኖቤል ሰላም ሽልማት ቀርበው ነበር።     


1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now