የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የ2020 ኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነ

*** የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአሸናፊት የበቃው ረሃብና የምግብ ዋስትና እጥረትን በመላው ዓለም በመፋለም ላበረከታቸው ጥረቶቹ ነው

Nobel Peace Prize

The United Nations World Food Programme won the Nobel Peace Prize on Friday. Source: Website

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የዘንድሮው የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአሸናፊት የበቃው ረሃብና የምግብ ዋስትና እጥረትን በመላው ዓለም በመፋለም ላበረከታቸው ጥረቶቹ ነው። 

ሽልማቱን ከኦስሎ ይፋ ያደረጉት የኖቤል ኮሚቴ ሰብሳቢ ቤሪት ሪስ-አንደርሰን ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ "በዚህ ዓመት ሽልማት የኖቤል ሰላም ሽልማት ኮሚቴ የዓለምን ዓይኖች በረሃብ እየተሰቃዩ ወይም ተጋልጠው ያሉቱ ሚሊየን ሰዎች ላይ እንዲያርፉ ይፈልጋል" 

"የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዋስትናን የሰላም መሳሪያ በማድረግ በመልቲዮሽ ትብብር ቁልፍ ሚና ተጫውቷል" ብለዋል።

ለዘንድሮው የኖቤል ሰላም ሽልማት በተወዳዳሪነት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕንና የኒውዝላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደንን አካትቶ 211 ግለሰቦችና 107 ድርጅቶች ቀርበዋል። 

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዲሴምበር 10 - 2020 በሚካሄደው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ወቅት 10 ሚሊየን ክሮና ወይም $1.1 ሚሊየን ጥሬ የአሜሪካን ዶላርስና የወርቅ ሜዳል ይቀበላል። 

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 97 ሚሊየን ሰዎችን በ88 አገራት በየዓመቱ እየረዳ ቢሆንም አሁንም በመላው ዓለም ከዘጠኝ ሰዎች አንዳቸው የሚመገቡት በቂ ምግብ የሌላቸው መሆኑን አስታውቋል።

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now