የዓለም ቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች የአውስትራሊያ ቪዛ ተሰረዘ

*** ባለፉት 24 ሰዓታት ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 34,994 ቪክቶሪያ ውስጥ 21,997 ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቁ

News

Serbian tennis star Novak Djokovic. Source: Getty

ሰርቢያዊው የቴኒስ ሻምፒየን ኖቫክ ጆኮቮች ወደ አውስትራሊያ የመግቢያ ቪዛ መመዘኛዎችን ባለሟሟላቱ የቪዛ ስረዛ ገጥሞታል።

ትናንት ረቡዕ ምሽት 11:30 pm ሜልበርን ቱላማሪን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው ጆኮቪች ለአውስትራሊያ ኦፕን ቴኒስ ሻምፒዮን ግጥሚያ የሚያበቃውን ቪዛ ባለመያዙ ወደ መጣበት እንዲመለስ የሚደረግ መሆኑ ተነግሯል።

ሆኖም የቴኒስ ኮከቡ ጠበቆች በአንድ የሜልበርን ፍርድ ቤት የይግባኝ ማመልከቻ እንደሚያስገቡ አመላክተዋል።

የቪክቶሪያ መንግሥት ለጆኮቪች ስፖንሰር እንዲሆን ተጠይቆ ፈቃደኛ አልሆነም። 

ጆኮቪችን ወደ ሜልበርን እንዳይዘልቅ አግዶ የያዘው የአውስትራሊያ የድንበር ኃይል ባወጣው መግለጫ " ዜግነት አልባ የሆኑና ይሁንታ የሌለው ቪዛ የሌላቸው ወይም ቪዛቸው የተሰረዘባቸው በእገታ ቆይተው ከአውስትራሊያ እንዲለቁ ይደረጋል" ሲል አስታውቋል። 

በሌላ በኩል የኖቫክ ወላጅ አባት ልጄ አላግባብ ታግቷል ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፤ የሰርቢያ ፕሬዚደንት አሌግዛነር ቩቺች በፊናቸው በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ማለዳ ላይ ከጆኮቪች ጋር በስልክ እንደተነጋገሩ ጠቅሰው "የኛ ባለስልጣናት በዓለም ምርጥ በሆነው የቴኒስ ተጫዋች ላይ የሚደርሱትን ትንኮሳዎች በተቻለ መጠን በፍጥነት ለመግታት ሁሉንም አይነት እርምጃዎች እየወሰዱ ናቸው።  ሰርቢያ ለኖቫክ ጆኮቪች፣ ለፍትሕና እውነት ትፋለማለች ። ኖቫክን እስከማውቀው ድረስ አይበገሬ ነው" ብለዋል።   

 

***

ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ ውስጥ የኮቪድ-19 የሆስፒታል ሕመምተኞች ቁጥር አሻቅቧል። 

እስከ ትናንት ረቡዕ 8pm ድረስ 1,609 ሰዎች ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተከታተሉ ሲሆን፤ 131 በፅኑ ሕመምተኛ ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 631 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምና ላይ ሲገኙ 100 በፅኑዕ ሕመምተኛ ክፍሎች እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለፉት 24 ሰዓታት 34,994 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል፤ ስድስት ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 21,997 ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ፤ ስድስት ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now