ኦ ካትሪን !!!

ኢትዮጵያ ሰማሽ ጉድሽን ? ሞት የሚሉት አረመኔ _ ሲነጥቃት ካቲን ቀኝሽን

Oh, Cathreine

Source: Courtesy of PD

ኢትዮጵያ ሰማሽ ጉድሽን ?

ሞት የሚሉት አረመኔ _ ሲነጥቃት ካቲን ቀኝሽን

 

ከልጆችሽ ያጣሽውን _ ሞራል እና ቅድስና

ካለም ጫፍ ከሺዎች ማይሎች _ በፈለቀች ካተሪና

 

በአጉል ስርአተት ባጉል ልማድ 

የሴት ልጆችሽ ክብር _ በድንቁርና ሲናድ

ባደባባይ ሲነወሩ _ ስብእናቸው ሲካድ

 

ባገራቸው በቀያቸው _ አላንስ ብሎ ስቃያቸው

ተነውረው ተገልለው _ አላልቅ ብሎ ሰቆቃቸው

ጠፍቶ በከና ሚላቸው

 

ማ ነበር ካጠገባቸው ? ማ ነበር ለህመማቸው ?

አዳኝ ሆኖ ተስፋ ሆኖ _ ያዳናቸው ያከማቸው

እንደ ባልንጀሮቻቸው _ እንደኩያ ጓዶቻቸው

ለሴት ክብር ያበቃቸው _ ለእንስት ወግ ያደላቸው

 

ኦ ካትሪን !!!

 

የኛ እመቤት

የኛ ቅድስት

አንቺን ፈጣሪ ባይሰጠን

ባንታደል ባያድለን

ይሄን ጊዜ ማን ነበርን?

ተገልለን ከጉባኤው _ ተነጥለን ከእድሩ

እንደ ምስኪን ግፉእ አሳ _ እንደ ወጣ ከባህሩ

አላንስ ብሎ ህመማችን

ባፍረት አለም መኖራችን

አልነበር ወይ ኑረታችችን ?

ባትኖሪልን ካትሪና _ ባትደርሺልን እናታችን

 

ኦ ካትሪን !!!

 

እናታችን

ኦ ካትሪን ቅድስታችን

 

ስብእናሽ ሰው ያረገን

ርህራሄሽ ያተረፈን

 

እስኪ ዛሬ እንጠይቅሽ _ ምን የሚሉት መባረክ ነው ?

ከናታችን ልጆች አጥተን _ ካቲ ካንቺ የታደልነው

 

ምን ይሆን ምስጢርሽ ከቶ _ ከኢትዮጲያ ያፋቀረሽ ?

ከልጆቿ ያጣመረሽ ?

 

እናውቃለን እናታችን _ ርህራሄ ነው አናድክምሽ

ሰውነት ነው ካትሪና _ ያንቺ አድማስሽ ያንቺ አገርሽ

ቆዳ አይደለም ደም አይደለም _ በጎነት ነው ማንነትሽ

ፍቅር ነው ያንቺ ከተማ _ ስብእና ነው ብሄርሽ

 

ካቲ ልበል ኬቲ ልበል _ እንዴት ብዬ ላቆላምጥሽ ?

እንደምን ፍቅሬን ልንገርሽ _ እንደምን ልሰናበትሽ ?

 

ኦ ካትሪን !!!

 

የኛ እመቤት

የኛ ንግስት

 

ስንለይሽ ቅጥ የለውም _ ልክ የለውም ሀዘናችን

በገነት ይሁን ማደሪያሽ _ ሰላም እረፍት እናታችን

 

ኦ ካትሪና !!!


2 min read

Published



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now