የኦነግ ሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ ጥቃት ማድረሱንና የአፀፋ እርምጃም መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ

*** "በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሽብር ጥቃት በመፈጸም ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል" - የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በትናንትናው ዕለት በኦነግ ሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ጥቃት በመፈጸም ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጉን ገለጠ፡፡

ክልላዊ መንግሥቱ "በዜጎች ህይወት ላይ በደረሰው ግድያ እና በዚህ የጭካኔ እና አሰቃቂ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል"ሲልም አክሎ አስታውቋል።

አያይዞም በወቅቱ በተወሰደ አፋጣኝ ክትትልና እርምጃ የተወሰኑ ጥቃት ፈጻሚዎች በክልሉ ኃይል መደምሰሳቸውንም አመልክቷል። 

ጥቃት ፈጻሚው ቡድን "በገጠርና በከተማ ባለስልጣናትና ዜጎችን የሚገድል ቡድን በማሰማራት በርካታ የሽብር ጥቃቶችን አድርሷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በርካታ የመንግስት እና የዜጎችን ንብረት አውድሟል" በማለትም ቀደም ሲሉ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አጣቅሶ ገልጧል። 

ለሕዝብ ባቀረበው ጥሪም "ይህ ሀይል የብተና እና የመጨራረስ ምኞት ያለው እና ከሀገር ግንባታ በተቃራኒው የሚቆም በመሆኑ ሕዝባችን በሁሉም ቦታ ተደራጅቶ የጥፋት እቅዱ እንዲመክት" ሲል ያሳሰበ ሲሆን፤ በየጊዜው በክልሉ በተከታታይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንም ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጧል።


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now