SKIP TO MAIN CONTENT

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ በደህንነት ስጋት ከካንብራ የመንግሥት መኖሪያ ቤታቸው ጥለው ወጡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመኖሪያቸው 6:00pm ላይ ወጥተው ወደ ሌላ ሥፍራ እንዲዛወሩ ግድ የተሰኙት ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ተከስቷል በሚል ጥርጣሬ ነው።

gettyimages-2259555108-612x612.jpg
Australian Prime Minister Anthony Albanese. Credit: BAY ISMOYO/AFP via Getty Images

1 min read

Published

By Kassahun Negewo

Source: SBS


Skip to article content

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካንብራ መኖሪያ ቤት በፖሊስ ፍተሻ ሲደረግበት ቆይቷል።

የአውስትራሊያ ፌዴራል ፖሊስ ምንም እንኳ ቀደም ሲል የደህንነት ስጋት ያሳደረ ሁኔታ አለ የሚል ማስጠንቀቂያ የደረሰው ቢሆንም፤ በፍተሻው ምንም አስጊ ሁኔታ ባለመከሰቱ አቶ አልበኒዚ ከምሽቱ 9:00pm ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስታውቋል።

አክሎም "በአሁኑ ወቅት በሕዝብ ወይም በማኅበረሰብ አባላት ላይ የተደቀነ ስጋት የለም። ተጨማሪ መረጃዎች አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ይሰጣል" ብሏል።

በቅርብ ወራት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩና በርካታ የምክር ቤት አባሎች ላይ ዛቻዎች ተሰንዘረዋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now