የመልካም አርአያ ተምሳሌዎች የፆታ - ተኮር ጥቃትን መግታት ይችላሉ

የወጣት ሰዎች ባሕሪዎች በአብዛኛው የሚቀረፁት በአዋቂዎችና በዙሪያቸው ባሉ ተከባካቢዎቻቸው ነው። ከከበሬታ ቢስ ባህሪይ በመቆጠብና በመልካም አርአያ ተምሳሌ አስተምህሮት በመታነፅ የአመፅ አዙሪትን መክላት እንችላለን።

Side view of young mother embracing young boy in studio

It’s never too young or never too late to talk to your children about respect Credit: Cavan Images/Getty Images

አንኳሮች
  • "ከመነሻው ይግቱት" ዘመቻ ትልሞቹ አዋቂዎችበወጣቶች ላይ በጎ ተፅዕኖዎች እንዲኖራቸው በማበረታት የአመፅ አዙሪትን መግታት ነው
  • ሰበብ ማብዛትን ትተን ልጆችን ከበሬታ ስለተመላበት ባህሪይ እናስተምር
  • በውይይቱ ለመሳተፍ የሚረዳዎት አጋዥ የመረጃ ምንጮች አሉ
"ወንዶች - ወንዶችን ነው የሚሆኑት" ወይም "ምንም አይደል ስለሚወድሽ እኮ ነው" የሚሉ ልጃገረዶችን ወይም ሴቶችን ዝቅ የሚያደርጉ አባባሎችን ለምን ያህል ጊዘ ሰምተዋል?

አባባሎቹ ጎጂ መስለው ባይታዩም ልብ ሳንላቸው የወንዶች ጠበኝነት አስባቡ የሴቶች ተንኳሽነት እንደሁ የማመሰሉ ሁነት አዘቦታዊ ሆኖ እንዲለመድ እናደርጋለን ሲሉ የመስኩ ጠበብት ያሳስባሉ።

ሁሉም ዝቅ አድራጊ ባህሪያት ወደ አመፅ አይመሩም፤ ይሁንና በሴቶች ላይ አመፀን መፈፀም የሚጀመረው ግና ከዝቅ አድራጊ ባህሪያት ነው። አዙሪቱን ከመነሻው በመግታት መክላት ይቻላል።

የ “ከመነሻው ይግቱት” ዘመቻ ምንድነው?

ከመነሻው ይግቱት ዘመቻ የአውስትራሊያ መንግሥታት ምክር ቤት ተነሳሽነት ሲሆን፣ ዓላማውም የፆታ ተኮር ጥቃትን አዙሪት ለመስበር ነው።

ዘመቻው የተጀመረው በሴቶችና ሕፃናት ላይ የደርሱትን ጥቃቶች የያዘ ስታቲስቲክስ በ2016 ይፋ ከሆነ በኋላ ነው።

እንደ አውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ አባባል፤
  • ከሶስት ሴቶች አንዳቸው ከ15 ዓመት ዕድሜያቸው አንስቶ በቅርበት በሚያውቁት ሰው የአካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ናቸው።
  • ከአራት ሴቶች አንዳቸው ያህል ከ15 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ ቢያንስ የስሜት ጉዳት አግኝቷቸዋል።
በአማካይ በየ10 ቀኑ አንዲት ሴት በአሁኑ ወይም በቀድሞ ፍቅረኛዋ እንደምትገደል እናውቃለን
የማኅበራዊ አገልግሎቶችና የቤተሰብ አመፅ ቅድመ መከላከል ሚኒስትር ደኤታ፤ ጀስቲን ኢሊየት
“የጥቃቱ መጠን እየቀነሰ እንዲዘልቅ የማድረጊያው ብቸው መንገድ የፆታ ኢ- እኩልነትና የአድልዎ ወይም ተመጣጣኝ ዕድል ያለማግኘት ክስተቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ሲቻል ነው" በማለት የማኅበራዊ አገልግሎቶችና የቤተሰብ አመፅ ሚኒስትር ደኤታ ጀስቲን ኢሊየት ለ SBS ተናግረዋል።

የወጣት ሰዎች ባህሪይ ላይ ተፅዕኖዎች የሚያድሩትና የሚቀረፁት በዙሪያቸው ባሉ አዋቂዎች፣ ተከባካቢዎችና ተፅዕኖ አሳዳሪዎች መሆናቸውን በመገንዘብ፤ ዘመቻው ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 17 ያሉ ልጆች ወላጆችና የቤተሰብ አባላት የራሳቸውን ባህሪይ ልብ ብለው እንዲመለከቱና የመልካም አርአያነት ተምሳሌ እንዲሆኑ ዒላማው አድርጓቸዋል።

የአመፅ አዙሪትን መገንዘብ

Inspired Children መፅሐፍ ደራሲና የወላጅነት ተጠባቢ የሆኑት ዶ/ር ሮዚና ማክአልፓይን “አመፅ ያድጋል እንጂ አይጀምርም” ይላሉ። .

የቤት ውስጥ አመፅ ከአያታቸው ወደ አባታቸው የዘለቀበት ቤት ውስጥ ያደጉት ዶ/ር ማክአልፓይን የአመፅ አዙሪትን ራሳቸው ኖረውት አልፈዋል።

“አባታችን ዲሲፕሊን፣ ግርፊያ መልካም ልጆችን ቀጥቶ የማሳደጊያ መንገድ ነው ብሎ ከሚያምነው ትውልድ ነው።"
Դժգոհ աղջնակ մը կ'ուլայ քրոջ հետ կռուելէ ետք
Past generations believed that discipline and corporal punishment was the way to raise good kids. Credit: FluxFactory/Getty Images
ቅጣቱም የቀበቶና የአርጩሜ ግርፊያን ወይም "ብርቱ እጆችን" ያካትታል” ሲሉ ያነሳሉ።

ገላቸው ላይ አርፎ ያለውን ሰንበር ለመሸፈን በበጋ ወቅት ሱሪዎችንና አጣብቂኞችን ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መሔዳቸውን ያስታውሳሉ።

“ይሁንና በዚያን ወቅት ማንም ሰው ምንም አይልም፤ ለእኛ በማኅበረሰባችን ውስጥ የተለመደ ነገር ነው።

“በእዚያ ሁኔታ ውስጥ አያሌ ሰዎች ያንን ይፈጽማሉ፤ በርካታ አግባብነት የሌላቸውን ነገሮች መማር ይኖራል። እንደ ልጅነታችን የቤተሰብ ሕይወት ምን እንደሁ፣ ተቀባይነት ያለውና የሌለው ምን እንደሁ፤ ትክክለኛውና ትክክለኛ ያልሆነው የቱ እንደሆነ እንቀስማለን።”

እንዲህ ያለውን አዙሪት ለመስበር አዋኪ የሚያደርገውም እንደ ዶ/ር ማክአልፓይን አባት ያሉና አመፅ የሚፈፅሙ በርካታ ሰዎች ጨዋ ልጆችን የማሳደጊያው ትክክለኛው መንገድ ያ ነው ብለው የሚያምኑ መሆኑ ነው።

ስለሆነም፤ አመፁ ይቀጥላል ሌላ መንገድ አያውቁምና ሲሉ ማክአልፓይን ያስረዳሉ።
ወጣት በነበርኩበት ወቅት እኔም አንደ አባቴ እሆን ይሆን ብዬ እጨነቅ ነበር። በርካታ ዓመታትን ምርምር በማድረግና አጋዥ ወላጅነት በማጋራት አሳለፍኩ። የቤተሰቤን የአመፅ አዙሪትም ሰበርኩ።
ዶ/ር ሮዚና ማካልፓይን፣ የወላጅነት ተጠባቢና የ 'Inspired Children' ደራሲ

ሰበብ ማብዛትን ያቁሙ

ልጃገረዶችን ከብር የመንሳት ወይም የጠበኝነት ባህሪያትን ማሳየትን አስመልክቶ ሰበብ መስጠት በወጣቶች ዘንድ የተቀባይነት አተያይ ሊቀርፅ ይችላል።

የሰበብ ተርጓሚ በዘመቻው ድረገፅ ላይ ቋንቋ እንደምን ድብቅ ትርጓሜን ሊይዝ እንደሚችል ያሳያል።

እናም ጎጂነት የሌለው የሚመስለው "ወንዶች - ወንዶችን ነው የሚሆኑት" አባባል ምናልባትም በልጃገረዶች ዘንድ "ወንዶች የሚሆኑት እንዲያ ነው፤ መቀበል ግድ ይለኛል" ወይም በወንዶች ልጆች ዘንድ "እኛ እንዲያ ነን፤ ምንም አይደል" የሚል ትርጓሜን ሊያሳድርባቸው ይችላል።

ዶ/ር ማክአልፓይን ይህን አስመልክተው ሰበቦችን መቀበል የለብንም፤ ልጆችን ከበሬታ ስለተመላው ባህሪይ ማስተማር አለብን ይላሉ።
Mother comforting son at home
Parents and carers have the responsibility to educate children about respect Credit: MoMo Productions/Getty Images

ንቁ፣ ግልፅ፣ ዘላቂ ውይይት ያድርጉ

ወ/ሮ ኢሊየት የዘመቻው አንዱ አካል የሆነውን “ከበሬታ የተመላበት ግንኙነትና የፆታ እኩልነት ውይይትን ንቁ፣ ግልፅና ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል ያበረታቱ”

“ውይይቱን መጀመሩ ጠቃሚ ነው" ይላሉ።

ከበሬታ ቢስነትንና ጠበኝነትን አስመልክቶ ከልጆች ጋር መወያየት ቀላል ጉዳይ አይደለም። ይሁንና ወላጆችና ሞግዚቶች በጉዳዩ ላይ ለማውጋት፣ አብዝተውም ለመነጋገር ዝግጁ ሊሆን ይገባል።
ከልጆችዎ ጋር ለመነጋገር ከቶውንም በእጅጉ ትንሽ ወይም በእጅጉ የዘገየ አይሆንም
ዶ/ር ሮዚና ማክአልፓይን
በዘመቻው ከሚታደሉት የመረጃ ምንጮች አንዱ የመነጋገሪያ መምሪያ ነው። ከልጆች የሚመጡ ምላሾችን ለመቃኘትና አፀፋ ለመስጠት የወግ መጀመሪያ አጋዥ መሳሪያ ነው።
እንደ መምህራንና ወላጆች ላሉ በእያንዳንዱ ሁኔታ ሰበቦችን አለመደርደር ጠቃሚ ነው፣ ይልቁንም ያንን ትቶ ከበሬታ የተመላበት ባህሪይ ምን እንደሁ ያስተምሩ፤ ያወያዩ።
ዶ/ር ሮዚና ማክአልፓይን
ዘመዳሞች በሚጣሉበት ወቅት "ሰበቦችን" ደርድሮ ከማለፍ ይልቅ ቆም ብለው "ያ ትክክለኛ ባህሪይ ነበርን?" "ያ ከበሬታ የተመላበት ነበርን?" "አንተ/አንቺ ብትሆኑ ኖሮ ምን ይሰማችሁ ነበር?" ብለው ይጠይቁ ሲሉ ዶ/ር ማክአልፓይን ያሳስባሉ።

በተጨማሪም ወላጆችና የቤተሰብ አባላት የልጆችን የመከባበር አተያይ ለመለየትና ለንግግርም መነሻ እንዲሆናቸው የመከባበር ማጣሪያ ዝርዝር ተዘጋጅቶ ይገኛል።

ጉዳዮችን ባሕላዊ የስሜት ጥንቁቅነትን በተላበሰ መልክ ማንሳት

ወ/ሮ ኢሊየት በሴቶችና ልጆች ላይ የሚደርሰው የአመፅ መጠን በተለይም በባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባት ዘንድ እንዲሁም፤ በአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ ቡድናት ዘንድ ከፍ ያለ መሆኑን ያናገራሉ።

የባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባት መሪዎች እኒህን ጉዳዮች ባሕላዊ የስሜት ጥንቁቅነትን በተላበሰ መልኩ የማንሳት ሁነኛ ሚና አላቸው።

ማሪያ ዲሞፖሎስ፤ ቪክቶሪያ ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት አገልግሎት ሰጪ የሆነው የደኅንነትና እኩልነት ቦርድ ሊቀመንበር ናቸው።

በማኅበረሰባቱ ውስጥ ስለ ዋነኛ በሴቶችና ልጆች ላይ የሚደርስ የቤት ውስጥ አመፅ ቅድመ መከላከል ሲናገሩ "የባሕል ሚናን፣ የሠፈራ ሚናና መድብለባሕል በነዚህ ገጠመኞች ላይ የሚያሳድራቸው ተፅዕኖ ይኖር እንደሁ መገንዘብ" እንደሚገባ ልብ ያሰኛሉ።

ባሕላችንን ወይም እምነታችንን እንደ ጉድለት ከማንሳት ይልቅ እኒያን ማዕቀፎች ተጠቅመን እንደምን ጠንካራና ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማኅበረሰባችን ውስጥ ማከናወን እንችላለን? ብለን እንጠይቅ።
ማሪያ ዲሞፖሎስ፤ የደኅንነትና እኩልነት ሊቀመንበር
ከመነሻው ይግቱት ዘመቻ የመረጃ ምንጮች በነባር ዜጎችና በሌሎችም ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ አለ፤ በ ዘመቻ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል።

ዘመቻው ውጤታማ እየሆነ ነው

ከመነሻው ይግቱት በዚህ ዓመት ወደ አራተኛው ምዕራፍ ዘልቋል። በተካሔደው ግምገማ መሠረት 68 ፐርሰንት ያህል ሰዎች የዘመቻውን እንቅስቃሴ ፍሬ ሃሳብ ልብ ብለዋል።

"ዘመቻውን ከተመለከቱት ውስጥ 82 ፐርሰንት ሰዎች ወጣቶች እንደምን ከበሬታ በተመላበት ሁኔታ ድርጊቶችን መፈፀም እንዳለባቸው የማስገንዘቡን ሚና ተረድተው ተቀብለዋል" ሲሉ ወ/ሮ ኢሊየት ገልጠዋል።

እናም፤ እስቲ ልጆቻችንን ስለ መከባበር ባህሪይ እናስተምር። የአመፅ አዙሪትን በመረዳት ከመነሻው መግታትና የመልካም አርአያ ተምሳሌም መሆን እንችላለን።

ድጋፍና አገልግሎቶች

1800RESPECT 1800 737 732 ወይም 1800respect.org.au

Lifeline 13 11 14 ወይም lifeline.org.au

ለሚኖሩበት ክፍለ አገርና ግዛት እዚህ ይጫኑ።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ጉዳት ደርስዎ ከሆነ 1800RESPECT በ 1800 737 732 ይደውሉ ወይም
1800RESPECT.org.au ድረገጽን ይጎብኙ። አጣዳፊ ከሆነ 000 ይደውሉ።


Share

Published

Updated

By Yumi Oba, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የመልካም አርአያ ተምሳሌዎች የፆታ - ተኮር ጥቃትን መግታት ይችላሉ | SBS Amharic