SKIP TO MAIN CONTENT

"ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል" - ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

*** የሰማሁት ዜና ልቤን ሰብሮታል ብል ማጋነን አይሆንም፤ የዛሬ ዓመት የተናገርኩት ከመድገም ዉጪ ሌላ ቃላት የለኝም፡፡

President Sahle-Work Zewde
President Sahle-Work Zewde Source: PD

1 min read

Published


Skip to article content

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ አስመልክቶ ፕሬዚደንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ የልባቸውን በኃዘን መሰበርና የሕግ የበላይነት መከበርን ግድ ማለት ያሰመረ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

"የሰማሁት ዜና ልቤን ሰብሮታል ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ የዛሬ አመት የተናገርኩት ከመድገም ዉጪ ሌላ ቃላት የለኝም፡፡

"ዘርና ሀይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሀን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል: ለቅሶ፣ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል ሃዘናቸው ሃዘኔ/ሃዘናችን ነው::

ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል፡ አገራችንን ካንዣበበባት ክፉ አዳጋ ለማዳን ሁላችንም ሚና አለን፡የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው፡ቀይ መስመር መጣስ የለበትም እንበል::"


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now