የአውስትራሊያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ በፅኑ የሳምባ ሕመም በ79 ዓመቷ ለህልፈተ ሕይወት ለበቃችው ድምፃዊት ጁዲት ዱርሃም ሐዘኑን በመግለጥ ላይ ነው።
የጁዲት እህት ቤቨርሊ ሺሃን ጁዲት በሕይወት ተደሳች፣ ሁሌም በተስፋ የተመላችና ቸር እንደነበረች ተናግራለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚም በበኩላቸው ጁዲት የአገር ቅርስና የአውስትራሊያ መለያ መሆኗን ሐዘናቸውን በገለጡበት ወቅት ጠቅሰዋል።
ጁዲት የተወለደችው ኢሰንደን - ቪክቶሪያ ነበር።
***
በአውስትራሊያ የቻይና ኤምባሲ አውስትራሊያ ከዩናይትድ ስቴትስ - ታይዋን ውዝግብ ራሷን እንድታገል አሳሰበ።
ኤምባሲው በቤጂንግ ላይ ጣትን መጠቆም ተቀባይነት እንደሌለውም አስገንዝቧል።
ለኤምባሲው ማሳሰቢያ አስባብ የሆነው የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ የዩናይትድ ስቴት ስ አፈ ጉባኤ የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ ቻይና የወሰደችው እርምጃ "ተመጣጣኝ ያልሆነ" እና "መረጋጋትን አደፍራሽ" ነው ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ሴናተር ዎንግ በአሁኑ ወቅት ከቻይናው አቻቻእው ዋንግ ዪ ጋር በካምቦዲያ የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበራት 47ኛ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ይገኛሉ።