“መጪዎቹ ዓመታት ስኬትን ለነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ ድምፃቸውን በሰጡት ሰዎች ልክ ሳይሆን፤ የምን ያህል ሰዎች ሕይወቶች እንደተለወጡ የምንመዝንበት እንደሚሆኑ ተስፋ አለኝ" ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ የአውስትራሊያን ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ለማከል የሚያስችሉና የኡሉሩ መግለጫን ሙሉ በሙሉ ግብር ላይ ለማዋል ሂደት አስጀማሪ የሆኑ ሶስት ረቂቅ የሕዝበ ውሳኔ ነጥቦችን ይፋ አደረጉ።

News

Prime Minister of Australia Anthony Albanese walks with Yolngu community during Garma Festival 2022 at Gulkula on July 29, 2022 in East Arnhem, Australia. Source: Getty

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ የነባር ዜጎች ድምፅ ዕውን እንዲሆን የሚወሰዱ ቀዳሚ እርምጃዎችን ይፋ ያደረጉት የጋራማ ፌስቲቫል በተከበረበት ጋልኩላ - ሰሜናዊ ግዛት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

በንግግራቸውም 'ቀላል' ረቂቅ የሕዝበ ውሳኔ ጥያቄ አቅርበዋል። 

“ቀጥተኛ ሃሳብ። ቀላል መርህ። ከልብ የመነጨ ጥያቄ" ብለውታል።
"የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ድምፅን የሚያቋቁም የሕገ መንግሥት ማሻሻያን ይደግፋሉ?"
ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኒዚ ለሕገ መንግሥቱ ማሻሻያ የመነጋገሪያ ነጥቦች ይሆኑ ዘንድም ሶስት መነሻ አርፍተ ነገሮችን አስቀምጠዋል፤

  1. የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ድምፅ ተብሎ የሚጠራ አካል ይኖራል።
  2. የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ድምፅ በፓርላማና የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ ዘንድ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ሕዝብ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ውክልና ይኖረዋል። 
  3. ፓርላማውም ለዚህ ሕገ መንግሥት ተገዢ ይሆናል፣ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች ድምፅ ስብጥር፣ ተግባራት፣ ስልጣንና አፈፃፀምን አስመልክቶ ሕጎችን የማውጣት ስልጣን ይኖረዋል።
አቶ አልባኒዚ አገሪቱ የሚጠብቃትን ምርጫ አስመልክቶ የሚኖሩ ማናቸውንም ስህተት አዘል ግንዛቤዎችን ለመክላት አጋጣሚውን በመጠቀም፤ አውስትራሊያውያን "የሰዎችን ሕይወት በማሻሻልና ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል" መካከል አንዳቸውን ካንዳቸው ለይተው መምረጥ እንደማይኖርባቸው ሲያመላክቱ፤

"ሁለቱንም መከወን እንችላለን – ያንንም ማድረግ አለብን” ብለዋል።
News
Australian Prime Minister Anthony Albanese has his face painted during the Garma Festival at Gulkula on July 29, 2022 in East Arnhem, Australia. Source: Getty
አክለውም፤
ምክንያቱም - ለ121 ዓመታት የጋራ ብልፅግናው መንግሥታት በትዕቢት በመመላት ለነባር ዜጎች የሚያሻውን የሚያውቁት እነሱ እንደሆኑ በማመን መፍትሔዎች ብለው የጫኗቸው ዛሬ ላለንበት ሁነት ዳርጎናል።
“ይህ የአቅመቢስነት ስቃይ፤ የ20 ዓመታት በሕይወት የመኖር የዕድሜ ልዩነት ክፍተት፣ በዓለም የእሥራት መጠኑ ከፍቶ የበዛ መሆን፣ ለነጭ አውስትራሊያውያን ከምናባዊ ዕይታቸው ባሻገር የሆነ የደዌ ሸክም። ቢሊየን ዶላሮችን አቃጣይ የተሰበረ ሥርዓትና አመኔታ ሊያሳድሩበት ለሚገባቸው ሰዎች በእጅጉ አናሳ አቅርቦት ያደረገ።"

“እናም መንግሥት የተሻለውን የማውቀው እኔ ነኝ በሚል ሙጥኝ ብሎ የሚቀጥል ከሆነ፤ ነገሮች የከፉ ይሆናሉ" ሲሉ አሳስበዋል።

ብሩህ ተስፋ ለስኬት

አቶ አልባኒዚ በሕይወት ዘመናቸው ውስጥ ስለገጠሟቸው "የላቁና ሐሰት" የተመላባቸው የለውጥ ጊዜያትን በምልሰት አንስተዋል። በማንም ያልተያዘ መሬት ዕሳቤን አሌ ከማለት እስከ የተሰረቁ ትውልዶች ብሔራዊ ይቅርታ፣ የክፍለ አገራትና ግዛቶች ወደ እውነት ነገራ እና የቃል ኪዳን ውል ጉዞ፣ የነባር ዜጎች ለፓርላማ አባልነት መብቃትና በሚኒስትርነት ማዕረግ ማገልገልን በዋቤነት ነቅሰዋል።
News
Linda Burney, Minister for Indigenous Australians embraces Australian PM Anthony Albanese during the Garma Festival at Gulkula on July 30, 2022 in East Arnhem. Source: Getty
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሕዝበ ውሳኔው ለስኬት መብቃት ያላቸውን "ብሩህ ተስፋ" ሲያመላክቱም፤

“እዚህ ጋርማ ተሰባስበን ሳለን መጪዎቹ ዓመታት ስኬትን ለነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ ድምፃቸውን በሰጡት ሰዎች ልክ ሳይሆን፤ በነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ የምን ያህል ሰዎች ሕይወቶች እንደተለወጡ የምንመዝንበት እንደሚሆኑ ተስፋ አለኝ"

“የማኅበረሰባት ለራስ ወሳኝነት መብቃት፣ የተፈጠሩ መልካም ዕድሎች፣ ለፍትሕ የበቁ ብይኖች፣ በመላ አገራችን ለነባር ዜጎች ያስገኛቸው ደህንነት"

“በእኔ በኩል ይህ ታላቅ ፕሮጄክት ለስኬት እንዲበቃ ላፍታም አላመነታም። እንዲሁም በትህትና፣ በተስፋ አብሮ ለመሥራት። እርግጠኛ ነኝ እንችላለን" ብለዋል።


 

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo, Rachael Knowles

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service