SKIP TO MAIN CONTENT

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ተመሠረተ

*** "ፕሮፌሰር መስፍን ሙሉ ህይወታቸውን ለአገር የሰጡ ናቸው" ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ - የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ሊቀመንበር

Community
Prof Mesfin Woldemariam. Source: ISA

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ራዕይና ስራዎች የሚያስቀጥል ፋውንዴሽን ተመሠረተ።

የኘሮፌሰሩ ዕረፍት አንደኛ አመት መታሰቢያና የፋውንዴሽኑን ምስረታ አስመልክቶ አዘጋጅ ኮሚቴው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህ ወቅት የፋውንዴሽኑ ሊቀመንበር ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ እንዳሉት ፕሮፌሰር መስፍን ሙሉ ህይወታቸውን ለአገር የሰጡ ናቸው።

ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ከድህነት የተላቀቀች፣ ሰላም፣ ሰብአዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ለማድረግ ሲሰሩ እንደነበር ገልፀዋል።

በስማቸው የተመሰረተው ፋውንዴሽን በማኅበረሰብ ሳይንስና በሠብዓዊ መብት ላይ ምርምር ለሚያካሂዱ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

ፋውንዴሽኑ ዓመታዊ አውደ ጥናት በማዘጋጀት የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲካሄዱ ያደርጋልም ተብሏል።

(ኢዜአ)


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now