SKIP TO MAIN CONTENT

በአማራ ክልል ከተሞች ዘር ተኮር ጥቃቶችን የሚፃረሩ ሰልፎች ተካሄዱ

*** "ጉዳት አድራሾች፣ ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ የታጠቁ አጥፊ ቡድኖችና ሃይሎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ አልያም መደምሰስ ይገባቸዋል" አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

"በአማራ ሕዝብ ላይ የደረሱትን ዘር ተኮር ጥቃቶች እንቃወማለን" በማለት በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፎኞች ተምመዋል።

 የተቃውሞ ሰልፎቹ የተካሔዱት በባሕር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልዲያ እና ሌሎችም የክልሉ ከተሞች ነው፡፡ 

 በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎቹ፤ በአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ ግድያዎች በአስቸኳይ እንዲገቱ፣ መንግሥት የአማራ ነገድ ተወላጆች ጥቃትና መፈናቀል ሊያሳስበውና እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ የሚጠይቁ ድምፆች በአፅንኦት ተስተጋብተዋል።

Rally
Source: EPA

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ - የአማራ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ በሰሜን ሸዋና አካባቢው ሰሞኑን ተከስቶ የነበሩትን ችግሮች አስመልክተው በተለይ ለኢፕድ በሰጡት መግለጫ መለስተኛ የጸጥታ መሻሻሎች መኖራቸውንና የተኩስ ድምፆች መቆማቸውን አስታውቀዋል።

አክለውም "ጉዳት አድራሾች፣ ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ የታጠቁ አጥፊ ቡድኖችና ሃይሎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ አልያም መደምሰስ ይገባቸዋል፤ ይህንን ለመስራት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋሉ' ብለዋል፡፡ 

 

 

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now