ከሐሙስ ኦክቶበር 5 / መስከረም 24 አንስቶ የተሻሻለው አዲሱ የስርጭት ጊዜ ሰሌዳ የሚጀምረው SBS Radio 1, SBS Radio 2, SBS Radio 3 እና SBS PopDesiን አካትቶ በመደበኛና ዲጂታል ኦዲዮ የአየር ስርጭት መስመሮች ነው።
የጊዜ ሰሌዳ ለውጦች
አማርኛ ቋንቋን አካትቶ የተወሰኑ ፕሮግራሞች ወደ SBS ሬዲዮ 3 ተዛውረዋል።
የፕሮግራሞቹን ዝግጅቶች ቀጥታ ስርጭት ቀን ላይ ሲሆን፤ ምሽት ላይ እስካሁን እየተላለፉ ባሉባቸው SBS ሬዲዮ 1 እና SBS ሬዲዮ 2 በድጋሚ መሰራጨታቸውን ሳያቋርጡ ይቀጥላሉ።.
በአዲሱ ስርጭት መሠረት ቀን ላይ በቀጥታ በ SBS ሬዲዮ 3 የሚተላለፉ ፕሮግራሞች አማርኛ፣ በርማ፣ ዲንካ፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ኮሪያ፣ ሳሞኣን፣ ሶማሊኛ፣ ስዋጂሊ፣ ትግርኛ እና ታይ ናቸው።
የፕሮግራሞቹን የቀን ስርጭቶች በድጋሚ እስካሁን በሚሰራጩባቸው መደበኛ ሰዓቶች የሚተላለፉ ሲሆን፤ የአማርኛ ፕሮግራም ድጋሚ ስርጭትን ሰኞና ዓርብ (ከ10:00-11:00 pm) በ SBS ሬዲዮ 1 ማድመጥ ይችላሉ።

የእኔ ፕሮግራም ስርጭት ላይ መሆኑን እንደምን ማወቅ እችላለሁ?
ቋንቋ | የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም | ድጋሚ |
አማርኛ | SBS ሬዲዮ 3፤ ሰኞ እና ረቡዕ 12:00PM | SBS ሬዲዮ 1፤ ሰኞ እና ዓርብ 10:00PM |
የማድመጫ መንገዶች
እና SBS ኦዲዮ ኧፕ ማድመጥ ይችላሉ። የ SBS Audio Appን ለ iOS በ App Store በኩል ለ Android በ Google Play አማካይነት መጫን ይችላሉ።
እንዲሁም፤ የተመረጡ የ SBS አማርኛ ፖድካስት እና ሬዲዮ ዝግጅቶችን የኧፕል ፖድካስቶች ጨምሮ በ LiSTNR, Spotify እና TuneIn አማካይነት ማድመጥ ይቻልዎታል።
የ SBS Radio 1 ስርጭትን AM ፍሪኩየንሲ ሜልበርን፣ ሲድኒ፣ ካንብራና ኒውካስትል፤ በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ በሌሎች ዋነኛ ከተሞች በመላ አውስትራሊያ በ AM ፍሪኩየንሲ ይተላለፋል።
SBS ሬዲዮ 3 ዲጂታል በመሆኑ፤ አድማጮች DAB+ ዲጂታል በኩል የ SBS ሬዲዮ ጣቢያዎችን ከሲድኒ፣ ካንብራ፣ ሜልበርን፣ አደላይድ፣ ፐርዝ፣ ዳርዊን፣ ሆባርት እና ብሪስበን ማድመጥ ይችላሉ።
በዲጂታል ሬዲዮዎ ለማድመጥ 'SBS Radio' የሚለውን ፈልገው እስኪያገኙ ወደ ፊትና ወደ ኋላ አለዋውጠው በማግኘት ያድምጡ።
አጠቃላዩ የ SBS አዲሱ የስርጭት ፕሮግራም ዕለተ ሐሙስ ኦክቶበር 5 / መስከረም 24 ቢጀምርም የአማርኛ ፕሮግራም አዲሱ የድጋሚ ስርጭት ኦክቶበር 6 / መስከረም 25፤ የቀን ቀጥታ ስርጭት ሰኞ ኦክቶበር 9 / መስከረም 28 እኩለ ቀን ላይ ይሆናል።