SKIP TO MAIN CONTENT

አሥመራ ላይ ስድስት ፍንዳታዎች ደረሱ

*** ስለ ፍንዳታዎቹ መግለጫ ያወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መንሰኤውን ወይም ፍንዳታዎቹ የደረሱባቸውን ሥፍራዎች አልጠቀሰም

Eritrean President Isaias Afwerki
Eritrean President Isaias Afwerki Source: AAP

1 min read

Published

Updated


Skip to article content

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እሑድ ባወጣው መግለጫ የኤርትራ መዲና አሥመራ ላይ ስድስት ፍንዳታዎች መከሰታቸውን አስታውቋል።

ይሁንና "ኖቬምበር 28 ስድስት ፍንዳታዎች አሥመራ ውስጥ 10:30 p.m ላይ ተከስቷል" ያለው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ደረሱ ስላላቸው ፍንዳታዎች መንሰኤና ሥፍራዎቹን አልጠቀሰም።

ሆኖም አሜሪካውያን ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል እየተካሄድ ስላለው ሁኔታ ልብ እንዲሉ አሳስቧል።

ቀደም ባሉት ሳምንታት ለሁለት ጊዜያት ያህል በሕወሓት የተወነጨፉ ሮኬቶች አሥመራ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው የሚታወስ ነው።

ለጊዜው ከኤርትራ መንግሥት በኩል ይፋ መግለጫ አልተደመጠም።  

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now