ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

*** አቶ ታገሰ ጫፎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆኑ

Homeland Report

Ethiopia's newly appointed Prime Minister Abiy Ahmed. Source: D.Kebede

በዛሬው ዕለት ጉባኤውን የጀመረው አዲሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርጧል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አዲሶቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም ቃለ መሃላ ፈፀመዋል።

በኢትዮጵያ የአዲስ መንግሥት ምስረታ መርኃ ግብር መካሄድ ጀምሯል።

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤያቸውን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ጀምረዋል።

አዲስ የምክር ቤቱ አባላት የምክር ቤቱ የምስረታ ጉባኤ እያከናወኑ ሲሆን አፈጉባኤ  አቶ ታገሰ ጫፎን በማድረግ ሰይመዋል።

ቃለ መሃላ ፈፅመው ወደ መድረኩ የወጡት አቶ ታገሰ ጫፎ "ለሰጣችሁ ኃላፊነትና ኢትዮጵያን እንዳገለግል ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ" ብለዋል።

ምክር ቤቱ በምክትል አፈጉባኤነት የቀድሞዋን የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ን ሾሟል።

በዚህ የመክፈቻ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር የሚያደርጉ ይሆናል።

ምክር ቤቱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተወዳድሮ አብላጫ ወንበር ያገኘው ብልፅግና ፓርቲ የሚወክለውን ዕጩ ለምክር ቤቱ በማቅረብ፣ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ያሰይማል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


1 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now