ሱዳን በዘንድሮው ጎርፍ የሕዳሴ ግድብ ምንም ተፅዕኖ እንዳላሳደረ ገለጠች

*** ከ500 ሺህ በላይ የአማራና አፋር ክፍለ አገራት ነዋሪዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተነገረ

GERD

GERD. Source: S.Bekele

የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በዚህ ዓመት በተከሰተው ጎርፍ ተፅዕኖ እንዳልነበረው አስታውቃለች።

የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ በቲዊተር ገጻቸው " የሕዳሴ ግድብ የተናጠል ሙሌት እንዳለ ሆኖ... ግድቡ በዚህ ዓመት ጎርፎች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም። ይሁንና ከሙሌቱ በፊት የመረጃ እጥረት ስለነበር ሱዳንን ከፍ ያለ ወጪን የሚጠይቅ ብርቱ ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ያለው ቅደመ ጥንቃቄ እንድታደርግ ግድ አሰኝቷል" ብለዋል። 

ሱዳን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ምርት ተጠቃሚ እንደምትሆንም ያላትን ተስፋ ገልጣለች።

ሱዳንና ግብፅ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው አለመግባባትን ተመርኩዞ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው መፍትሔ ለማፈላለግ ጉዳዩ በአፍሪካ ኅብረት ተይዞ ይገኛል።    

ኢትዮጵያ በፊናዋ ከሕዳሴ ግድብ ከፍ ያለ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨትና የልማት ግቦቿንም ለማሳካት ያላት ተስፋ ከፍ ያለ መሆኑን እያመላከተች ነው። 

ሰላም አስከባሪ ኃይል

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ካላት የድንበር ግጭት ጋር ተያይዞ በተባበሩት መንግሥታት ጊዜያዊ የፀጥታ ሓይል ስር ተሰማርቶ ያለው የኢትዮጵያ ጦር ከአወዛጋቢው የአቢዪ ክፍለ አገር ለቅቆ እንዲወጣ ጠየቀች።

ጥያቄዋም በመንግሥታቱ ድርጅት በኩል ተቀባይነት በማግኘቱ አቢዪ የሚገኘው 3000 ኢትዮጵያ ጦር በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተጠናቅቆ የሚወጣ ይሆናል። 

የኢትዮጵያ ጦር ከደቡብ ሱዳን የአገር ምስረታ ሕዝበ ውሳኔ ጀምሮ አብዪ በሰላም አስከባሪ ኃይልነት ተሰማርቶ ይገኛል።   

የኢትዮጵያ ጦር ከሌሎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በተውጣጣ ጦር ይተካል። 

 የአፋርና አማራ ተፈናቃዮች

 

የሰላም ሚኒስትርና የብሔራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባሪያ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሕወሓት በፈጸመው ጥቃት በአፋርና አማራ ክልል ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ገለጹ።

 በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በሰብአዊ ድጋፍ እየተንቀሳቀሱ ላሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አጋር አካላት በሰብአዊና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

 ሚኒስትሯ በዚህ ወቅትመንግስት ወደ ትግራይ የሚያስገቡ አራት መንገዶችን ሲጠቀም የነበረ ቢሆንም ህወሓት በከፈተው ጥቃት መስመሮቹ መዘጋታቸውን ገልጸዋል።

 እስካሁን ከህልውና ዘመቻው ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ለሰብአዊ ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

 በአማራ ክልል ብቻ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ጠቁመው፥ አሁን ላይ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት።

 መንግስት በትግራይ ክልል በ47 ወረዳዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት አድርጓልም ብለዋል ሚኒስትሯ።

 ከዚህ ባለፈም እስካሁን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ 321 ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን ጠቁመዋል።

 (FBC)


2 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now