4ኛው የጣና ማኅበራዊ ሚዲያ ሽልማት “ትኩረት ለጤና ፤ ትኩረት ለጣና” በሚል ተካሄደ

*** የSBS አማርኛ የኢትዮጵያ ኮርስፖንደንት ደመቀ ከበደና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ ከተሸላሚዎቹ መካከል ይገኙበታል

Social Media Awards

Obang Metho (L) and Deemeke Kebede (R) Source: Supplied

ሽልማቱ በባህር ዳር ጣና ሃይቅ የተካሄደ ሲሆን፣ የዘንድሮ ሽልማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዘርፎች በመቀነስ በጤና እና በጣና ዙሪያ በተለያዩ ዘርፎች በማቀናጀት ዕውቅናና ሽልማት የመስጠት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።

Social Media Awards
Source: Supplied

በዚህም መሰረት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢዘዲን ከሚል፣ በጤና መረጃ -  ሸጋው ማሬ፣ በፈጣን፣ በወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃ- ደመቀ ከበደ፣ በጣና ሃይቅ አካባቢ ልማት መረጃ ዘርፍ- ተዋቸው ደርሶ፣ በበጎ አድራጎትና በሰብዓዊ መብት መረጃ- ኦባንግ ሜቶ እና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ በጤና ዘርፍ በተቋም ደረጃ ልዩ ተሸላሚ- የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ተሸላሚ ሆነዋል።

Social Media Awards
Obang Metho Source: Supplied

የሰብዓዊ መብት መረጃ ዘርፍ ተሸላሚው ኦባንግ ሜቶ በሽልማቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር “ጣናን ከእንቦጭ ራሳችንን ከጥላቻና ዘረኝነት ማጽዳት ይኖርብናል” ብለዋል፡፡


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now