ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሣሁን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች እየተፈፀሙ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መባባሳቸው እንደሚሳስበው በፌስቡክ ገጹ ገለጠ፡፡
ጥቃቶቹ የማያባሩና እየተባበሱ መምጣታቸውን የገለጸው አርቲስቱ ይህን እየተባባሰ የመጣውን ጥቃት ኃላፊነት ያለበት የመንግሥት አካል ለማስቆም ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡

ቴዲ አፍሮ “የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበት” መንግሥት ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስቧል፡፡
Share

