39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

AU.jpg

A scene of the 39th Leaders Summit of the African Union (AU) at the AU headquarters in Addis Ababa, the capital of Ethiopia, on 14 February, 2026. Credit: D.Kebede

ጉባኤው " ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በመካሄድ ላይ ያለው።

መሪዎቹ የሚመክሩት 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አሥፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ ውይይት በተደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ ነው።

የውሃ ደህንነት እና የንጽህና፣ አጠባበቅ፣ የአጀንዳ 2063 ትግበራን እና አህጉራዊ ትስስር፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ ተቋማዊ እና የፋይናንስ ማሻሻያዎች፣ ቀጣናዊ አጋርነት እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና ከአጀንዳዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ።

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ እስከ ነገ የሚካሄድ ይሆናል።

ትናንት ምሽት የኢትዮጵያ መንግሥት ለተሳታፊዎች በብሔራዊ ቤተ መንግስት የእንኳን ደህና መጣችሁ የእራት ግብዣ አከናውኗል።

( ደመቀ ከበደ ፡ ከአፍሪካ ሕብረት )


1 min read

Published

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now