"አድዋ የራሳችንን ዕድል በራሳችን መወሰን እንደምንችል ያረጋገጠ ድል ነው" — የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማኅሙድ አሊ ዩሱፍ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ ባስተላለፉት መግለጫ አድዋ የአፍሪካውያን የጋራ ኩራትና የነፃነት ፋና መሆኑን ገልፀዋል።

AdwaAA.jpg

Credit: PD

ሊቀመንበሩ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ፣ እ.ኤ.አ በ1896 የተመዘገበው የአድዋ ድል አፍሪካውያን የቅኝ ግዛትን ቀንበር ሰብረው የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት ታሪካዊ ክስተት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

"አድዋ የአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ክብር እና አንድነት የታየበት ታላቅ አሻራ ነው" ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ድሉ አኅጉሪቱ ዛሬ ለምትከተለው "አጀንዳ 2063" እና "ለተባበረች አፍሪካ" ርዕይ ዋነኛ መሠረት መሆኑን አመላክተዋል።

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ አክለውም፣ አፍሪካውያን ዛሬ የሚገጥሟቸውን ዘመናዊ ተግዳሮቶች ለማሸነፍ ያ ድል ያስገኘውን የአንድነትና የፅናት መንፈስ ሊላበሱ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም ኅብረቱ የ2025ቱን ዓመት "የካሳ ክፍያ ዓመት" በማድረግ ላለፉት በደሎች ፍትህ ለመጠየቅ የሚያደርገውን ጥረት አድዋ ትልቅ ሞራል እንደሚሰጠው ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በመላው አህጉሪቱ ሰላምን ለማስፈን፣ የኢኮኖሚ ውሕደትን ለማፋጠን እና የጋራ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።


1 min read

Published

By Demeke Kebede

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now