የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ተገባደደ

*** “ዛሬ ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓ/ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል" - ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

GERD

GERD Source: S.Bekele

ሁለቱን ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት የሚያስችለው ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ውኃ መሙላቱን መንግስት አበሰረ

በርካቶች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰሱን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጉባ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት የደስታ መግለጫ “ዛሬ ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓ/ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል። ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ”  ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም  “ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና ይዘናል ማለት ነው ፣ ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና እንዴት እያገዘን እንደሆነ መረዳት እንችላለን። ለዚሁም ምስጋና ይግባው። እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው ዓመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል። በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን” ብለዋል፡፡

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]


1 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now