አንኳሮች፤
- በወላጅና አስተዋጽዖ አበርካች (ቋሚ ነዋሪ) ወላጅ ዘርፍ መካከል ያሉ ልዩነቶች የአፈጻጸም ሂደትና የቪዛ ክፍያዎች ናቸው።
- በኤፕሪል 2019 በተሻሻለው ስፖንሰር የተደረገ (በጊዜያዊነት) ወላጅ (ንዑስ መደብ 870) ቪዛ መሠረት ወላጆች አውስትራሊያ ውስጥ እስከ 10 ዓመታት እንዲቆዩ ያስችላል።
- እያንዳንዱ የመጤ ፕሮግራም ቪዛ ፈቃድ በዓመት ጣራ የተወሰነ ነው
የአውስትራሊያ ዜጎች፣ ቋሚ ነዋሪዎችና መመዘኛዎችን የሚያሟሉ የኒውዚላንድ ዜጎች ወላጆቻቸውን በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ወደ አውስትራሊያ ማስመጣት ይችላሉ።
ሁለት የቪዛ ዘርፎች አሉ – ‘ወላጅ’ እና ‘አስተዋፅዖ አበርካች ወላጅ’።
የ ‘አስተዋፅዖ አበርካች ወላጅ’ ዘርፍ በጣሙን ውድ ነው።
ከጁላይ 1 እስከ ጁን 30 በሚካሔደው በእያንዳንዱ 'ዓመታዊ የመጤ ፕሮግራም' በርካታ ቪዛዎች ይታደላሉ።
በብሪስበን The Migration Place የመጤ ተወካይና ጠበቃ ዘኬ ቤንትሊ፤ መጠነኛ የክፍያ ዋጋ ያላቸው ቪዛዎች ተፈላጊነታቸው ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ይሁንታን ለማግኘት ሂደቱ እስከ 30 ዓመታት እንደሚፈጅ ያስረዳሉ።
በሌላ በኩል ግና፤ ቤተሰቦች በአንድ ወላጅ 45,000 እና 55,000 የአውስትራሊያ ዶላርስ ለመክፈል ከቻሉ ከሁለት እስከ አምስት ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ቪዛ ማግኘት ይችላሉ።
"አዝጋሚው መንገድ እጅጉን አዝጋሚ ነው። ከ 18 እስከ 30 ዓመታት ይፈጃል።"

Smiling multi-generation Asian family Source: Getty Images
ወላጆች ከሌላ አገር ይልቅ አውስትራሊያ ውስጥ በቋሚነት የሚኖሩ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ልጆች ካላቸው የቤተሰብ ሚዛን መመዘኛን ያልፋሉ።
"ሶስት ልጆች ያለዎት ከሆነ፤ ሁለቱ አውስትራሊያ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውና የሚኖሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።"
በኤፕሪል 2019 ስፖንሰር ያላቸው ወላጅ (በጊዜያዊነት) (ንዑስ መደብ 870) ቪዛ በመንግሥት የማሻሻያ ለውጥ ተደርጎበታል።
Sirus Migration Lawyers ተወካዩ ሳም ጃዛዪሪ፤ በአዲሱ ጊዜያዊ ቪዛ መሠረት ወላጆች አውስትራሊያ ውስጥ ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ተደራርቦም እስከ 10 ዓመት ጣራ መቆየት ይችላሉ።
ያም አመልካቾችን ከልጆቻቸው ወይም ከልጅ ልጆቻቸው ጋር እስከ አሥር ዓመታት አብረዋቸው እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።
የእኒህ ቪዛ ዋጋም 5000 ለሶስት ዓመታት 10,000 እስከ አምስት ዓመታት ያስቆያል።
ቪዛውን ለማግኘት የሚፈጀው ጊዜም እስከ አራት ወራት የሚደርስ ሲሆን፤ ስፖንሰር ማድረግ የሚቻለውም ከባልና ሚስቱ የአንዳቸውን ወላጆች ብቻ ይሆናል።
ስፖንሰር የተደረገ ወላጅ (በጊዜያዊነት) (ንዑስ መደብ 870) ቪዛ፤ አውስትራሊያ ውስጥ ለመሥራት አይፈቀድለትም ወይም ለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት አይችልም።
ከአሥር ዓመታት በኋላ ወደ መጡበት አገር መመለስ ይኖርባቸዋል።
በጥቅሉ ከወላጆች ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችሉ ሰባት ዓይነት ቪዛዎች አሉ።

A grandson kissing his grandmother Source: Getty Images
እያንዳንዱ የቪዛ አሰጣጥ ግና በመጤ ፕሮግራም ዓመት የመቆያ ጊዜ ገደብ የተጣለበት ነው።
ከጁላይ 1,2019 እስከ ጁን 30,2020 ሁሉም የወላጅ ቪዛ ዓይነቶች ተደምረው የተፈቀዱት ቪዛዎች 7,371 ናቸው።
በእያንዳንዱ የመጤ ፕሮግራም ዓመት 15,000 ስፖንደር የተደረገ ወላጅ (በጊዜያዊነት) ቪዛዎች በታካይነት ይሰጣሉ።
አንዴ የቪዛ መጠን ገደብ ላይ ከተደረሰ በኋላ ግና የኢሚግሬሽንና ድንበር ጥበቃ ዲፓርትመንት በሚቀጥለው ጁላይ 1 የመጤ ፕሮግራም ዓመት እስከሚጀምር ድረስ ቪዛዎችን መስጠቱን ይገታል።
Share

