Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራቹ አማን ፍስሃጽዮን ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ ተወዳጅ ከሆኑ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ኢቢኤስ ቴሌቪዥንን መሥርተው በሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ አማን ፍስሀጽዮን ሕይወታቸው ማለፉን ሚዲያቸው ኢቢኤስ አስታውቋል።

Amman Fitssehazion.png
The late Amman Fissehazion, CEO of EBS Television. Credit: EBS

በኢቢኤስ ዘገባ መሠረት አቶ አማን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ረቡዕ የካቲት 4 ቀን 2018 ከእዚህ ዓለም ተለይተዋል።

አቶ አማን የኢትዮጵያ ብሬድካስተሮች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉም ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢቤኤስ ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ እና መስራች አማን ፍስሃጽዮን ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መልዕክት÷ 'የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍስሃጽዮን በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል' ብለዋል፡፡

አማን ለኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከነበራቸው አንዱ ነው በማለት አስታውሰዋል።

'ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፈች ጊዜ ሁሉ የሚጠበቅበትን አድርጓል' በማለት አውስተዋቸዋል፡፡


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now