SKIP TO MAIN CONTENT

"ሰብአዊነትና ፍቅር ለትግራይና ለመተከል" አስተባባሪ ቡድን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ማስባሰቡን አስታወቀ።

*** የአስተባባሪ ቡድኑ ሰብሳቢ አርቲስት ታማኝ በየነ በዓይነት በተደረገ ድጋፍ ግምቱ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው እርዳታ መገኘቱን ገልጧል።

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

"ሰብአዊነትና ፍቅር ለትግራይ እና ለመተከል" በሚል ሀሳብ ስር ጥምረት በመፍጠር የድጋፍ ማሰባሰብ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የቆየው ቡድን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የጥምረቱ ሰብሳቢ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹታማኝ በየነ ትናንት በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፤ በትግራይ እና በመተከል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተብሎ በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች 20 ሚሊዮን 716 ሺህ 559 ብር ገቢ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ በጎፈንድሚ በውጭ አገራት በተከፈተው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ደግሞ 210 ሺህ ዶላር መገኘቱን አስታውቋል።

በአይነት በተደረገ ድጋፍም ግምቱ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ርዳታ መገኘቱንም ታማኝ ገልጿል።

የተሰበሰበው ርዳታ ከዛሬ ጀምሮ ወደሁለቱም አካባቢዎች መጓጓዝ እንደሚጀምር አርቲስ ታማኝ በየነ አስታውቋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now