“አንድነታችንን ጠብቀን ያጋጠመንን የሕልውና አደጋ በትግላችን እንቀለብሰዋለን” የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

*** "የኮረምና አለማጣ አካባቢዎች በትህነግ እጅ ስር እንዲወድቁ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቋም የወሰደ መንግስታዊ ክፍል ስለመኖሩ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል" አብን

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

 

ትሕነግ "የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአንድ ወገን የወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያና በአማራ ክልል ህዝብ ላይ መሰረተ ሰፊ የሆነ ወረራና ጥቃት ማድረግ ጀምሯል" ሲል የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

 

የክልላዊ መንግሥቱ ይህን ያስታወቀው ሐምሌ 6 “አንድነታችንን ጠብቀን ያጋጠመንን የሕልውና አደጋ በትግላችን እንቀለብሰዋለን” በሚል ርዕስ ባወጣው ባለ ስድስት ነጥብ መግለጫ ነው።   

በባለ ስድስት ነጥብ መግለጫው፤

  • በየግንባሩ የሚገኙ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት፣ ሕዝባዊ ፖሊስና ሰላም አስከባሪ አባላትና ለየክልሉ የጸጥታ አካላት "የተሰጣችሁን ህዝባዊና አገራዊ ተልዕኮ በጽናትና በቁርጠኝነት እንደምትወጡ እምነታችን የጸና ነው" ሲል ጥሪ አቅርቧል
  • ጥሪው በዚህ ሳይወሰንም "መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በትህነግ ወያኔ ላይ የተጀመረው ሕግን የማስከበር ትግል ተጠነናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን እርብርብ ሁሉ ማድረግ አለበት ብለን እናምናለን" ሲል አገር አቀፍ የትብብር ጥሪ አድርጓል
  • ቀደም ሲል ስልጠና ላላቸውና በማንኛውም የመንግስት ጸጥታ መዋቅር ሲሰሩ ለነበሩ ሁሉ "በክልሉ ጸጥታ መዋቅር ውስጥ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እያቀረብን ከዛሬ ጀምሮ በየአካባያችሁ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ በፈቃደኝት እንድትመዘገቡ ለማሳሰብ እንወዳለን" ብሏል
  • ለክልሉ ወጣቶችም "ከማንኛውም ግብታዊ እንቅስቃሴ ታቅባችሁ በየደረጃው ለሚኖረው ምልመላና ስልጠና በመሳተፍ በቂ ዝግጅት አድርጋችሁ የመንግስትን ጥሪ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል
  • እንዲሁም ለክልሉ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ ማህበራዊ አንቂዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የትብብር ጥሪ አቅርቧል
  • በማከልም ለክልሉ ሕዝብ፣ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ለሚገኙ ምሁራንና የክልሉ ተወላጆች፣ በተለያየ ሙያ ተሰማርተው ላሉና የክልሉ ባለሀብቶች የትግሉ አጋር እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

አብን

 

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በበኩሉ ሐምሌ 6. 2013 ባወጣው መግለጫ  "የኮረምና አለማጣ አካባቢዎች በትህነግ እጅ ስር እንዲወድቁ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቋም የወሰደ መንግስታዊ ክፍል ስለመኖሩ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል" ያለ ሲሆን ዝርዝር ማብራራያዎችን ግና አላከለም።

 

ንቅናቄው "ከመነሻው ህዝባችን የፖለቲካ ቁማር ማስያዥያ እንዳይሆን በሚል ያልተቋረጠ ጥሪ ስናቀርብ ብንቆይም የተለያዩ አካላት በፈጠሩት ውዥንብርና የአመራር ክፍተት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዳግም ለህልውና አደጋ ተጋልጦ ይገኛል" በማለት በበርካታ ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ እንደተፈፀመ አመልክቷል።

 

አያይዞም፤ ታሪክ፣ ማኅበራዊ ክብርንና ሉዓላዊነትን አስተሳስሮ በማንሳት "በፖለቲካ ሸፍጥና በአመራር ክፍተት ምክንያት የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ለሚደረገው ሁለንተናዊ ዘመቻ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በደጀንነት ርብርብ እንዲደረግ ንቅናቄያችን ይሄን ታሪካዊ ጥሪ እያስተላለፈ፣ የህልውና ዘመቻውን በሙሉ እንዲቀላቀሉ እና እንዲያስተባብሩ ለሁሉም የንቅናቄያችን አባላትና አመራሮች ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን" ብሏል።

 

 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now