SKIP TO MAIN CONTENT

የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ

*** ወ/ሮ ኬሪያ ከአፈ ጉባኤነታቸው የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው ነበር

Keria Ibrahim
Keria Ibrahim (L) Source: Getty Images

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ እጃቸውን መስጠታቸው የመንግሥት የትግራይ ግብረ ኃይል "ከሕወሓት ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራር አባላት አንዷ የሆኑት ኬሪያ ኢብራሂም ለፌዴራል ኃይሎች እጃቸውን ሰጥተዋል" ሲል ገልጧል።

ወ/ሮ ኬሪያ በወርኃ ጁን ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መነሳታቸውን አስታውቀው ነበር።

የሳቸውን መግለጫ ተከትሎም ምክር ቤቱ "አፈ ጉባኤዋ ራሳቸው በጠሩት መደበኛ ስብሰባ ዋዜማ የሥራ መልቀቂያ ሳያስገቡ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን መግለጣቸው የምክር ቤቱን ደንብ ያልተከተለ ነው። የአፈ ጉባኤዋ ስንብትም የምክር ቤቱን ሂደት አያስተጓጉልም" ማለቱ ይታወሳል።

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now